Category: Uncategorized

Home of best apps

በሰከንድ 490 ሜጋ ባይት ፋይልን ለመላላክ የሚያስችለው ፈጣኑ የጎግል ጎ መተግበሪያ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጎግል ያለኢንተርኔት መረጃን ለመላላክ የሚያስችለው ጎ መተግበሪያው ላይ ማሻሻያ ማድረጉ ተነግሯል። ጎግል ጎ የተባለውን መተግበሪያውን ባሳለፍነው ዓመት ያስተዋወቀ ሲሆን፥ መተግበሪያውም የአንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም በሚጠቀሙ ስልኮች ላይ ነው የሚሰራው። መተግበሪያው በስልካችን ላይ ያሉንን መረጃዎች አስተካክለን ለመያዝ የሚረዳ ሲሆን፥ ያለኢንተርኔት ግንኙነትም በተወሰነ ክልል ውስጥ ላሉ ስልኮች የተለያዩ መረጃዎችን ለመላላክ ያገለግላል። በተጨማሪም…
Read more

ካርቦን ዳይ ኦክሳይድን ከአየር ውስጥ የሚሰበስበው ቴክኖሎጂ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የካናዳ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ለጤናችን ጎጂ የሆኑ ካርቦን ዳይ ኦክሳይድን ከአካባቢያችን አየር ውስጥ በቀላሉ የሚሰበስብ መሳሪያ መስራቱን አስታውቋል። ካርቦን ኢንጂነሪንግ የተባለው እና እንደ ቢል ጌትስ ካሉ ባለሀብቶች የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኘው ኩባንያው፥ ካርቦን ዳይ ኦክሳይድን ሰው ሰራሽ በሆነ መንገድ ከአካባቢ አየር ውስጥ እንዴት መሰብሰብ ይቻላል የሚለው ላይ ሲሰራ ቆይቷል። በዚህም በአየር…
Read more

ማየት የተሳናቸውን በምላሳቸው ማየት እንዲችሉ የሚያደርገው ቴክኖሎጂ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዓለም አቀፍ ደረጃ 258 ሚሊየን ማየተ የተሳናቸው ሰዎች እንዳሉ መረጃዎች የሚያመላከቱ ሲሆን፥ ቴክኖሎጂ ምስጋና ይግባውና በምላሳቸው ማየት የሚያስችላቸው ፈጠራ ይፋ ሆኗል ተብሏል። በዚህም የሰው ልጂን ስሜት የሚተኩ ሰው ሰራሽ መሳሪዎች እየተስፋፉ መምጣታቸውን ተከትሎ የሰው ልጆች በተለያዩ አጋጣሚዎች ያጧቸውን ስሜቶች ማጣጣም መቻላቸውም ነው የተገለጸው።  የእይታ መረጃዎችን ከአካባቢው በመሰብሰብ ማየት የተሳናቸው…
Read more

በራሱ ጊዜ ወደ መኪናነት መቀየር የሚችል ሮቦት ተዘጋጀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 18፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጃፓን ኢንጅነሮች ሰው መያዝ ሚችልና ወደ መኪናነት መቀየር የሚችል ሮሆቦት ማዘጋጀታቸውን ይፋ አደረጉ፡፡ በሮቦት የቴክኖሎጅ ፈጠራ ታሪክ የመጀመሪያው አስደናቂ ክስተት አንደሆነ ነው የተነገረው፡፡ ሁለት ሰዎችን የሚይዘው እና በደቂቃ ውስጥ ወደ ስፖርት መኪናነት የሚቀየረው ይህ ሮቦት 3 ነጥብ 7 ሜትር እንደሚረዝም ተነገሯል፡፡ ሮቦቱን ለማዘጋጀት የህፃናት አንሜሽን ፌልም መነሻ እንደሆናቸው አዘጋጆቹ…
Read more

ታላላቅ ኩባንያዎች የደንበኞች የመረጃ ነፃነት ጥበቃ ህግ ለማውጣት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከትራምፕ አስተዳደር ጋር እየመከሩ ነው

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 23፣ 2010 (ኤፍ.ቢሲ) ታላላቅ ኩባንያዎች የደንበኞች የመረጃ ነፃነት ጥበቃ ህግ ለማውጣት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከትራምፕ አስተዳደር ጋር እየመከሩ ነው ተብሏል። ምክረ ሀሳቡ የበይነ መረብ ተጠሚዎችን የመረጃ ነፃነት መብት ለማስከበር የሚያስችል ህግ ለማርቀቅ መሆኑ ነው የተገለጸው። በዚህም ባለፈው ወር ብቻ ከ80 ኩባንያዎች ከተውጣጡ ተወካዮች ጋር 22 ያህል ስብሰባዎች መካሄዳቸውን የሀገሪቱ የቴሌኮሚዩኒኬሽንና የመረጃ አስተዳደር…
Read more

ትዊተር በእስራኤል የሃማስና የሂዝቦላ የትዊተር አድራሻዎችን ዘጋ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 26 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ግዙፉ የማህበራዊ ትስስር ሚዲያ ትዊተር በእስራኤል አገልግሎት የሚሰጡ የሃማስና የሂዝቦላ የትዊተር አድራሻዎችን ዘግቷል። ኩባንያው እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የእስራኤል መንግስት ለኩባንያው ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ነው ተብሏል። የእስራኤል መንግስት በእስራኤል አገልግሎት የሚሰጡ የሁለቱ ቡድኖች የትዊተር አድራሻዎች ስጋት ሆነዋል ሲል ለኩባንያው አስታውቋል። የእስራኤል የሃገር ውስጥ የደህንነት ሚኒስትር…
Read more

ማይክሮሶፍት የመረጃ ማእከሉን ውቅያኖስ ውስጥ አስቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የመረጃ (ዳታ) ማእከላት ለዓለማችን የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ወሳኝ እየሆኑ ከመጡ ዋል አደር ብለዋል። የዳታ ማእከላት ከሌሉ የድረ ገፅ አገልግሎቶች፣ መረጃዎቻችንን ለመጠባበቂያነት የምናከማችባቸው እንደ ክላውድ ያሉ የመረጃ ማስቀመጫ ቋቶች አይኖሩም ነበር። ታዲያ እነዚህ የመረጃ ማከማቻ ማእከላት ስራቸውን ለመስራት እና ራሳቸውን ለማቀዝቀዝ ከፍተኛ የሆነ የኤሌክትሪክ ሀይል እንደሚጠቀሙም ይታወቃል።ይህ ደግሞ ለአካባቢ ብክለት…
Read more

የካርበን ጋዝን ለመሰብሰብ የሚያስችል ቴክኖሎጂ የሙከራ ትግበራ ላይ ሊውል ነው

አዲስ አበባ ግንቦት 13፣2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የብሪታኒያው ሊድ ዩንቨርሲቲ ከባዮ ጋዝ ሃይል ምንጭ የሚወጣ በካይ ጋዝ ወደ ከባቢ አየር እንዳይገባ ለመቆጣጠር የሚያስችል ቴክኖሎጂ አገልግሎት ላይ ለማዋል አየሰራ መሆኑ ተገለጸ ። ድራአክስ ሃላፊነቱ የተወሰ ኩባንያ የመጀመሪያውን የአዲሱን ፈጠራ የሙከራ ትግበራ በዚህ ወር በሰሜን ዮርክሺሬ የ ታዳሽ ሃይል የኤሌክትሪክ ሃይል ፕሮጀከት ጣቢያ አገልግሎት ላይ እንደሚያልም ታውቋል።  ቴክኖሎጂው በፈረንጆቹ 2009 የተገኘ የብሪታኒያው…
Read more

አንጎላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደህዋ ያመጠቀቻት ሳተላይት ስራ አቆመች

አዲስአበባ፣ ሚያዚያ 16፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) አንጎላ በሩሲያ እርዳታ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ህዋ ያመጠቀቻት ሳተላይት ስራ ማቆሟን አስታወቀች። አንጎሳት 1 በመባል የምትጠራው ሳተላይት ከካዛኪስታን ጣቢያ ወደ ህዋ የተላከችው ከአራት ወራት በፊት ነበር። 300 ሜትር ያህል የምትረዝመው ይህች ሳተላይት ወደ ህዋ የተላከችው ለመገናኛ አገልግሎት ለማዋል እንደነበር ተገልጿል። ሳታላይቷ የቴክኒክ እክል የገጠማት ከመጠቀች ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ሲሆን፥…
Read more

ፌስቡክ በቻይና ቢሮውን ለመክፈት አቅዷል

አዲስ አበባ፣ ሀምሌ፣18፣2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፌስቡክ አገልግሎቱን በማይሰጥባት ቻይና ትርፋማ በሆነው ገበያ ለመሳተፍ ፈቃድ በማግኘቱ ቢሮውን በቅርቡ እንደሚከፍተ ተገለፀ። ኩባንያው በቻይና የሚከፍተው ቢሮ ቻይናውያን አበልፃጊዎችና ስራ ፈጣሪዎችን ለመደገፍ የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል። በቻይና የሚከፈተው ይህ ቢሮ ለኩባንያው የመጀመሪያው እንደሚሆንም ነው የተነገረው። ቻይና በአለም አቀድ ደረጃ ከፍተኛ የሆነ የማህበራዊ መገናኛ ብዙሀን ንግድ ያለባት ቢሆንም ትዊተር፣ ፌስቡክ እና ዩቲዩብ…
Read more

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ ከሮቦቷ ሶፍያ ጋር ቆይታ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሶፍያ ከተባለችው ሮቦት ጋር በዛሬው እለት ቆይታ አድርገዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአይ.ሲ.ቲ ኤክስፖ ኢትዮጵያ 2010 ላይ የተገኘችውን ሮቦቷን ሲፊያ ነው በዛሬው እለት ያገኙት። ሶፊያ የተባለችው ሮቦት 67 በመቶ ፕሮግራም የተደረገችው እና የተሰራቸው በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ነው። በዚህ ወቅትም ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ…
Read more

የቻይናው ዜድቲኢ በአሜሪካ የተጣለበትን የ1 ቢሊየን ዶላር ቅጣት ሊከፍል ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቻይናው ግዙፉ የቴሌኮም ኩባንያ የሆነው ዜድቲኢ በዩናይትድ ስቴትስ የተጣለበትን የአንድ ቢሊየን ዶላር ቅጣት ለመክፈል ከሀገሪቱ ጋር መስማማቱ ተገለጸ፡፡ ኩባንያው ላይ ቅጣቱ ሊጣል የቻለው ሀገሪቷ ማዕቀብ ከጣለችባቸው ከኢራንና ሰሜንኮሪያ ጋር የንግድ ልውውጥ አድርጓል በሚል መሆኑ ተነግሯል፡፡ ኩባንያው ወደ ገበያ ከመግባቱ በፊት እንደ ማስያዣ ወይንም መንግስት ያስቀመጣቸው ቅድመሁኔታዎች እስኪሟሉ ድረስ እንዲሁም…
Read more