Category: Uncategorized

Home of best apps

አፕል እንደ መፅሃፍ የሚታጠፍ ስማርት ስልክ እየሰራ መሆኑ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ግዙፉ የስማርት ስክል አምራች አፕል ፊቱን ወደ ታጣፊ ስማርት ስልኮች ማዞሩ እየተነገረ ነው። ኩባንያው አዲስ እየሰራ ነው የተባለው አይ ፎን ስማርት ስልክ ልክ እንደ መፅሃፍ የሚታጠፍ እና የሚዘረጋ መሆኑንም መረጃዎች ጠቁመዋል። በእሲያ ሀገራት የሚገኙ በርካታ ጥሬ እቃ አቅራቢ ኩባንያዎችም ከአፕል ጋር በመሆን በታጣፊ ስማርት ስልክ ዙሪያ እየሰሩ መሆኑን አረጋግጠዋል…
Read more

ሳዑዲ አረቢያና ሶፍት ባንክ የዓለማችን ግዙፉን የፀሃይ የኃይል ማመንጫ በ200 ቢሊየን ዶላር ሊገነቡ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሳኡዲው ልዑል መሃመድ ቢን ሰልማን ሶፍት ባንክና ሳኡዲ አረቢያ በ200 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ከፀሃይ ብርሃን የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ (ሶላር) ሊገነቡ መሆኑን አስታወቁ፡፡ በአሜሪካ የሶስት ሳምንት ጉብኝት ላይ የሚገኙት ልዑል ቢን ሰልማን እቅዳቸውን ይፋ ያደረጉት በኒውዮርክ ነው፡፡ ፕሮጀክቱን ይፋ ባደረጉበት ወቅት አብረዋቸው የነበሩት የጃፓኑ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ስራ አስፈጻሚ ማሳዮሺ ሰን…
Read more

ቦይንግ የመረጃ መረብ ጥቃት እንደተቃጣበት አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ግዙፉ የአውሮፕላን አምራች ኩባንያ ቦይንግ የመረጃ መረብ ጥቃት እንደተቃጣበት አስታወቀ። ኩባንያው በተወሰነ የአሰራር ስርዓቱ ላይ እክል የፈጠረ የመረጃ መረብ ጥቃት እንደተፈጸመበት መለየቱን የኩባንያው ምክትል ፕሬዚዳንት ተናግረዋል። ምክትል ፕሬዚዳንቷ ሊንዳ ሚልስ እንዳሉት፥ የተፈጸመው ጥቃት የተወሰነ የአሰራር ስርዓቱ ላይ እክል ከመፍጠር ያለፈ ጉዳት አላደረሰም። በኩባንያው ላይ የተቃጣውን…
Read more

ቻይና ፊት በማየት ብቻ መላ ህዝቧን በአንድ ሰከንድ ውስጥ ማንነታቸውን የሚመዘግብ ቴክኖሎጂ ፈጥራለች

አዲስ አበባ መጋቢት 20፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና የክትትል ስርዓቷን ለማሻሻልና ለማሳደግ የሰው ማንነት በፊቱ መለየት የሚያስችል ቴክኖሎጂ መፍጠሯ ተነገረ። ይህ ስርዓት 1 ነጥብ 4 ቢለየኑን የቻይና ህዝብ በአንድ ሰከንድ እና የአለምን ህዝብ በ2 ሰከንድ ማወቅ ያስችላል ተብሏል። የሰውን ማንነት በፊት ማወቅ የሚያስችለው ይህ ስርዓት የክትትል ካሜራዎችን በቻይና ተደራሽ ለማድረግ በፈረጆንቾቹ 2005 የተከፈተው የስካይኔት…
Read more

ቴስላ 123 ሺህ መኪናዎቹን ጠራ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መቀመጫውን በዩናይትድ ስቴትስ ያደረገው ቴስላ የቴክኖሎጂ ኩባንያ በቴክኒክ ችግር ምክንያት 123 ሺህ መኪኖችን መጥራቱን አስታወቀ። የተጠሩት መኪኖች በአውሮፓውያን ከ2016 በፊት የተመረቱ ናቸው ተብሏል። የቴስላ ቃልአቀባይ መኪኖቹ ሊጠሩ የቻሉት ከዝገት ጋር በተገናኘ መሆኑን ገልፀዋል። እስካአሁን በተጠቀሰው ችግር አደጋ ያደረሰ መኪና የለም ተብሏል። ድርጅቱ ለሁሉም የመኪናው ተጠቃሚዎች ኢሜይል መላኩን ነው ያስታወቀው።…
Read more

በቻይና የኮንትሮባንድ ነጋዴዎች ድሮን በመጠቀም የሞባይል ስልኮችን ከሆንግ ኮንግ እያስገቡ ነው

አዲስ አበባ መጋቢት ፣21 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቻይና የሚገኙ የኮንትሮባንድ ነጋዴዎች ድሮኖችን በመጠቀም በህገወጥ መንገድ የሞባይል ስልኮችን ከሆንግ ኮንግ በማስገባት ላይ መሆናቸው ተነገረ። የኮንትሮባንድ ነጋዴዎቹ 78 ነጥብ 8 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የሚገመት ዘመናዊ ስልኮችን ከሆንግ ኮንግ ወደ ሸንዜን በመጠቀም ማስገባታቸው ነው የተገለፀው።   ሀገሪቱ በዚህም የተጠረጠሩ 26 ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውላለች። በቻይና ድሮን በመጠቀም ወንጀል ሲፈፀም…
Read more

በፊስቡክ ላይ መረጃዎቻቸው የተበረበረባቸው ተጠቃሚዎች 87 ሚሊየን ደርሷል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣2010 (ኤፍ. ቢ. ሲ) በካንብሪጅ አናላቲካ የፈስቡክ መረጃዎቻው የተበረበረባቸው ተጠቃሚዎች ቁጥር 87 ሚሊየን መድረሱን ፊስቡክ ይፋ አደረገ። ከዚህ በፊት የፈስቡክ መረጃቸው የተበረበረባቸው ተጠቃሚዎች ቁጥር 50 ሚሊየን እንደሆነ መነገሩ ይታወሳል። የግለሰቦች መረጃ እንዲበረበር የሚያስችለውን መተግበሪያ የሚጠቀሙት 270 ሺህ እንደሆኑ ቢነገርም ተጠቃሚዎቹ 305 ሺህ ናቸው ተብሏል። ይህን መተግበሪያ ከሚጠቀሙት 97 በመቶዎቹ አሜሪካውያን ሲሆኑ 16…
Read more

ኢትዮጵያ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን የዲጂታል የንግድ ምልክት ማሳወቂያ ድረገጽ ስራ አስጀመረች

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 27፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢፌዴሪ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽህፈት ቤት ቤት ዲጂታል የንግድ ምልክት ማሳወቂያ ድረገጽን አስመርቀ። ድረገጹ በድርጅቶች የተመዘገቡ የንግድ ምልክቶችን ለማሳወቅ የሚረዳ ሲሆን፥ ከዓለም የአዕምሮዊ ንብረት ድርጅት ጋር በመተባበር የተሰራ ነዉ ተብሏል። ድረገፁን መርቀው ስራ ያስጀመሩት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢኒጂነር ጌታሁን መኩሪያ የንግድ ምልክት…
Read more

አፕል ያለ እጅ ንኪኪ ትእዛዝ የሚቀበል ስልክን ይፋ ሊያደርግ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አፕል ኩባንያ የስልክ ስክሪን መስታወት ሳይነካ የሚፈለገውን አገልግሎት መስጠት የሚችል ስልክን ይፋ ሊያደርግ መሆኑ ተነገረ። ይህ ከላይ ወደ ታች የታጠፈ ስክሪን የሚኖረው ስልክ አፕልን በዘርፉ ተወዳዳሪ እንደሚደርግ ይጠበቃል። ይህ የአፕል ፈጠራ የስልኩን ስክሪን ሳይነኩ የእጅ ጣትዎን ወደ ስልኩ ብቻ በማቅረብ ስልኩን መጠቀም ያስችላል ተብሏል። ከዚህ በፊት ስክሪናቸው ጠርዝ ላይ…
Read more

ከዋትስአፕ ጋር ተመሳስሎ የተሰራ ሀሰተኛ መተግበሪያ የሰዎችን የግል መረጃ እየዘረፈ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከዋትስአፕ መተግበሪያ ጋር ተመሳስሎ የተሰራ የሀሰት መተግበሪያ የግለሰቦችን መረጃ ለመዝረፍ ጥቅም ላይ እየዋለ መሆኑ ተነግሯል። “ዋትስአፕ ፕላስ (WhatsApp Plus)” የሚል መጠሪያ የተሰጠው አዲሱ ሀሰተኛ መተግበሪያ በአሁኑ ወቅት በስፋት ኢንተርኔት ላይ የተለቀቀ መሆኑንም የአሜሪካ የኢንተርኔት ደህነንት ኩባንያ የሆነው ማልዌርባትስ የምርምር ማእከል አስታውቋል። እንደ ኩባንያው ገለፃ ሀሰተኛ መተግበሪያው ተጨማሪ የዋትስአፕ አገልግሎቶችን…
Read more

ፌስ ቡክ የካምብሪጅ አናሊቲካ ማስጠንቀቂያ ለተጠቃሚዎች እየላከ ነው

አዲስ አበባ ሚያዚያ 2፣ 2010፣ (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፌስቡክ የደንበኞች መረጃ በካምብሪጅ አናሊቲካ መበርበር አለመበርበሩን ማረጋገጥ የሚያስችል መልዕክት ለተጠቃሚዎች እየላከ ነው። ኩባንያው ለሁሉም የገጹ ተጠቃሚዎች ሁለት የተለያዩ መልዕክቶችን እያደረሰ ሲሆን፥ ደንበኛውም የፌስ ቡክ አድራሻው በተባለው ተቋም መበርበር አለመበርበሩን እንዲያውቅ ያስችለዋል።  ተጠቃሚዎቹ መልዕክቱ ሲደርሳቸው መረጃውን ለመበርበር ጥቅም ላይ የዋለው መተግበሪያ እና መተግበሪዎቹ ሊይዙ የሚችሉትን መረጃ ምን ሊሆን እንደሚችል…
Read more

ጂሜይል ማሻሻያ ሊደርግበት ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 4፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ጉግል ኩባንያ የኤሌክትሮኒክስ መልዕት መለዋወጫን(ጂሜይል) ለተጠቃሚዎች ምቹ ለማድረግና በአዲስ አቀራረብ ለማምጣት መሻሻያ ሊደረግበት መሆኑን አስታወቀ። ይህንንም ጉግል ጂ ስዊት አገልግሎትን ለሚጠቀሙ ደንበኞቹ ማሳወቁ ተነግሯል። ማሻሻያው ከሚያካትታቸው ጉዳዮች መካከል የጉግል ካላንደር በመልዕት መለዋወጫው ማግኘት ማስቻል ይገኝበታል። ከሚገቡ መልዕከቶች መካከል መልስ ያልተሰጣቸው መልዕክቶች እንዲሰጣቸው የማስታወስ ተግባርንም ያካትታል። እንዲሁም ከአንድ…
Read more