ካርበን ዳይኦክሳይድ ጋዝን ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችለውን ብረት በጥናት ማግኘታቸውን ተመራማሪዎች ገለጹ

Home of best apps

ካርበን ዳይኦክሳይድ ጋዝን ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችለውን ብረት በጥናት ማግኘታቸውን ተመራማሪዎች ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት27፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ካርበን ዳይኦክሳይድ ጋዝን ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችለውን ብረት በጥናት ማግኘታቸውን ተመራማሪዎች ገልጸዋል።

ተመራማሪዎቹ በዴላዋሬ ዩንቨርሲቲ ‘‘ቢስምዩዝ’’ በተባለው ብረት ላይ ባደረጉት ጥናት የካርበን ዳይኦክሳይድ ጋዝ መጠን ከከባቢ አየር ለመቀነስና በቀጣይነት የነዳጅ ምንጭ በመሆን ሊያገለግል እንደሚችል ማረጋገጣቸው ነው የተገለጸው።

አሁን ላይ ‘‘ቢስምዩዝ’’ ለጥይት፣ ጌጣጌጥና በአሲድ የማይጠቁ ቁሳቁሶችን ለማስራት አገልግሎት ላይ እንደሚውልም ዘገባው አመላክቷል።

‘‘ቢስምዩዝ’’ የተባለው ብረት ለየት ያለ ባህሪ ያለው ሲሆን፥ ከከባቢ አየር የካርበን ዳይኦክሳይድ ጋዝ መጠን በመቀነስ፣ ወደ ነዳጅ በመቀየር ለሰው ልጆች ምቹ አካባቢን በመፍጠርና ተመራጭ የኢንዳስተሪ ኬሚካሎችን ለማምረት ማስቻሉን የጥናት ቡድኑ በዴላዋሬ ዩንቨርሲቲ ቤተ ሙከራ ባደረገው ጥናት አረጋግጧል ተብሏል።

በጥናቱ ‘‘ኢሚዳዞሊየም’’ እና ‘‘አሚዲኒየም’’ በተባሉ የጨው ውህዶች በተነከረ ‘‘ቢስምዩዝ ፊልም’’ ውስጥ የኤሌክትሪክ ሀይይል እንዲያልፍ ሲደረግ ካርበን ዳይኦክሳይድን ወደ ‘‘ጋዞሊን’’ እና ‘‘ፈሚክ’’ አሲድ መቀየር መቻሉ ነው የተገለጸው።

በተመሳሳይ መልኩ በሌሎች የጨው ውህዶችና ‘‘ቢስምዩዝ ፊልም’’ ተመሳሳይ ውጤት ለማግኘት መቻሉንም ነው በጥናቱ የተመላከተው።

‘‘ጋዞሊን’’ እና ‘‘ፈሚክ’’ አሲድ የሰዎችና እንሰሳት ምግቦች ሳይበላሹ ለረጅም ጊዜ ለማቆየት፣ የፕላስቲክና ቆዳ ውጤቶችን፣ ሰው ሰራሽ ጣዕም እንዲሁም ሽቶዎችን ለምሰራት በግባዓትነት የሚያገለግሉ ናቸው ተብሏል።

ቀደም ሲል ተመራማሪዎች የተለያዩ ውህዶችን በቤተ ሙከራ ለመስራት በርካታ ውህደቶችን የሚያፋጥኑ ንጥረ ቅመሞችን ይጠቀሙ የነበረ ሲሆን፥ በዚህ ጥናት ግን አንድ ንጥረ ቅመም ብቻ አገልግሎት ላይ መዋሉን በዴላዋሬ ዩንቨርሲቲ የጥናቱ ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ጆኤል ሮሴንታል ገልጸዋል።

ጥናቱ በአይነቱ አዲስ ሲሆን፥ ከጸሃይ፣ ነፋስና ውሀ በተጨማሪ በታደሽ ሃይል ምንጭነት ሊያገለግል እንደሚችል ነው ዘገባው የሚያስረዳው።

 

 

 

ምንጭ፦ sciencedaily.com

የተተረጎመውና የተጫነው፦ በእንቻለው ታደሰ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *