ፌስቡክ የተጠቀሚዎችን መረጃ ለቴክኖሎጂ ቁስ አምራቾች አሳልፎ ሰጥቷል በሚል የቀረበበትን ክስ ውድቅ አደረገ

Home of best apps

ፌስቡክ የተጠቀሚዎችን መረጃ ለቴክኖሎጂ ቁስ አምራቾች አሳልፎ ሰጥቷል በሚል የቀረበበትን ክስ ውድቅ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፌስቡክ የተጠቃሚዎቹን የግል መረጃ ያለፍቃድ እና ያለአግባብ አፕልን ጨምሮ ለሌሎች የቴክኖሎጂ መገልገያ አምራች ኩባንያዎች አሳልፎ ሰጥቷል በሚል የቀረበበትን ክስ ውድቅ አደረገ።

ክሱን ኒው ዮርክ ታይም ጋዜጣ ያቀረበበት ሲሆን፥ ፌስቡክ ግን በክሱ ላይ የቀረበው መረጃ እውነት አይደለም ሲል ክሱን ውድቅ አድርጎታል።

ጋዜጣው ባወጣው ሪፖርት መሰረት ፌስቡክ ከ10 ዓመት በፊት ስራ ላይ ባዋለው ሶፈትዌር አማካኝነት ለአማዞን፣ አፕል፣ ብላክ ቤሪ፣ ማይክሮሶፍት እና ሳምሰንግ ከሚፈቀደው በላይ የተጠቃሚዎቹን የግል መረጃ ሲያቀብል ቆይቷል ብሏል።

እንደ ኒው ዮርክ ታምስ ጋዜጣ ክስ፥ ፌስቡክ እነዚህን መረጃዎች ያለ ተጠቃሚዎች እወቅ እና ያለ አግባብ ነው ሲያጋራ የቆየው።

የፌስቡክ የምርት ዘርፍ ምክትል ፕሬዚዳንት አይሜ አርኪቦንግ፥ ፌስቡክ ለተቋማቱ መረጃን እንደሚያቀርብ በመግለፅ፤ ሆኖም ግን ያለ አግባብ የግል መረጃን አሳልፎ ይሰጠጣል መባሉ ትክክል አይደለም ብለዋል።

ስለዚህ የቀረበው ክስ ትክክል አይደለም ሲሉ አጣጥለውታል ምክትል ፕሬዚዳንቱ።

ፌስቡክ ከዚህ ቀደምም ካምብሪጅ አናላቲካ የተባለው ተቋም የ87 ሚሊየን ተጠቃሚዎችን መረጃ አላግባብ እንዲበረብር አድርጓል የሚል በምርመራ ስር እንደሚገኝ አይዘነጋም።

ምንጭ፦ www.reuters.com

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *