ለአሽከርካሪዎች መረጃ የሚያቀብለው ስማርት የትራፊክ መብራት

Home of best apps

ለአሽከርካሪዎች መረጃ የሚያቀብለው ስማርት የትራፊክ መብራት

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለአሽከርካሪዎች ቀድሞ መረጃ የሚያቀብል ስማርት የትራፊክ መብራት በብሪታኒያ እየተሞከረ መሆኑ ተሰምቷል።

አዲሱ ስማርት የትራፊክ መብራት አሽከርካሪዎች ቀጣይ የትራፊክ መብራት አረንጓዴ በርቶ እያለ መድረስ እንዲችሉ በምን ያክል ፍጥነት ማሽከርከር እንዳለባቸው መልእከት የሚያስተላልፍ ነው ተብሏል።

ቴክኖሎጂው በኔትዎርክ አማካኝነት ለአሽከርካሪዎች መልእክቱን የሚያስተላልፍ መሆኑም ተገልጿል።

smart_trafick_light.jpeg

ይህም ተሽከርካሪዎች የትራፊክ መብራት ላይ ቆመው የሚያባክኑትን ጊዜ እና የሚለቁትን የካርበን መጠል ለመቀነስ የሚያስችል መሆኑም ተነግሯል።

የስማርት የትራፊክ መብራት ሀሳቡ የመነጨው በብሪታንያ ውስጥ ያለአሽከርካሪ ለሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ምቹ መንገድን ለመፍጠር ታስቦ እየተሰራ ባለ ፕሮጄክት ነው።

ፕሮጄክቱ የሙከራ ደረጃዎችን አልፎ ወደ ስራ በሚገባበት ጊዜም ለአሽከርካሪዎች ከሚፈጥረው እፎይታ በተጨማሪ፤ አካባቢንም ከአየር ብክለት ለመከላከል የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ ነው ተብሏል።

ምንጭ፦ www.huffingtonpost.co.uk

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *