አፕል የአይፎን ስልክን በመጠቀም ቤት እና መኪናን መቆለፍ እና መክፈት የሚያስችል አገልግሎት ሊጀምር ነው

Home of best apps

አፕል የአይፎን ስልክን በመጠቀም ቤት እና መኪናን መቆለፍ እና መክፈት የሚያስችል አገልግሎት ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት፣ 22፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ)አፕል ኤንኤፍሲ በተሰኘ ማሻሻያው ሰዎች በአይፎን ስልካቸው የቤት በሮችን፣ መኪናዎችን መክፈት እና መዝጋት የሚያስችላቸውን እንዲሁም የትራንስፖርት አገልግሎት ክፍያዎችን መፈፀም የሚያስችል አገልግሎት በቅርቡ ሊጀምር ነው።

ኤንኤፍሲ በተሰኘው እና በተሻሻለው የአይፎን የስልክ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ስልካቸውን በመጠቀም የቤት በሮችን መክፈት እና መዝጋት፣ መኪናዎችን፣ የህናፃዎችን የደህንነት ስርዓት መቆጣጠር ይችላሉ።

ከዚህ በተጨማሪ የጤና አገልግሎት እና የህዝብ ትራንስፖርት ክፍያዎችን በኢዲሱ የአይፎን ስልክ አገልግሎት ማግኘት ያስችላል ተብሏል።

የአፕል ኩባንያ ዋና መስሪያ ቤት ሰራተኞች አዲሱን የአይፎን ስልክ አገልግሎት በመጠቀም ቢሮዎች እና ህንፃዎች መክፈት እና መዝጋት እንዲችሉ አድርጓል።

ከዚህ በፊት ኩባንያው በአይፎን 6 እና አይፎን 6ኤስ ስልኮች ኤንኤፍሲ የተሰኘውን አገልግሎት በመጠቀም የመረጃ ልውውጥ፣ የተገደበ የአፕል ክፍያ እና የሞባይል ክፍያ አገልግሎቶችን ሲሰጥ እንደቆየ ተነግሯል።

የተሻሻለው የኤንኤፍሲ አገልግሎት ከብሎቱዝ በተሻለ ደህንነቱ የተረጋገጠ እንደሆነ ተጠቁሟል።

ይህ አገልግሎት በቀጣዩ ወር እንደሚጀምር የተገለፀ ሲሆን፥ የአይፎን ስልክ ተጠቃሚዎች ከተጠቀሱት አገልግሎቶች በተጨማሪ ከደህንነት ጋር ተያይዞ ላሉ ጉዳዮቸ ይህን አገልግሎት ለመጠቀም እድል ይፈጥራል ተብሏል።

የአፕል ኩባንያ የአይፎን ስልክ ኤንኤፍሲ አገልግሎት ለመጀመር ኤችአይዲ ግሎባል ከተሰኘ ኩባንያ ጋር ከፈረንጆቹ 2014 ጀምሮ ሲሰራ እንደቆየ ታውቋል።

ምንጭ፦ ቴክዋርም

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *