ግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ ከመረጃ መረብ ብርበራ ጋር በተያያዘ 120 ሺህ ዩሮ ቅጣት ተወሰነበት

Home of best apps

ግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ ከመረጃ መረብ ብርበራ ጋር በተያያዘ 120 ሺህ ዩሮ ቅጣት ተወሰነበት

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) ግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎቹን መረጃ ለመረጃ በርባሪዎች እንዲጋለጥ አድርጓል በሚል የ120 ሺህ ዩሮ ቅጣት ተወሰነበት።

የተማሪዎቹ መረጃ በፈረንጆቹ 2004 በዩኒቨርሲቲው አንድ የትምህርት ክፍል በተዘጋጀው አነስተኛ ድረ ገጽ ላይ የተጫነ እና ለመረጃ በርባሪዎቹ መጋለጡም ነው የተገለጸው።

 ይህ አነስተኛ ድረ ገጽ በወቅቱ ለሚሰጥ ስልጠና ከዩኒቨርሲቲው እውቅና ውጭ የተዘጋጀ ሲሆን፥ ተቋሙ የተማሪዎቹ መረጃ ለመረጃ መረብ በርባሪዎች እንዲጋለጥ አድርጓልም ነው የተባለው።

በዚህም ዩኒቨርሲቲው የ19 ሺህ 500 ተማሪዎችን መረጃ በዚህ ድረ ገጽ በመልቀቅ ለመረጃ በርባሪዎች እንዲጋለጥ ማድረጉን ተከትሎ ቅጣቱ ተወስኖበታል።

የተማሪ ስሞች፣ አድራሻ፣ የልደት ቀን፣ የስልክ ቁጥሮች፣ የፊርማ ናሙና እና አጠቃላይ የአካላዊ እና አዕምሯዊ መረጃዎች፥ በመረጃ መረብ በርባሪዎቹ ተጋልጠዋል።

ዩኒቨርሲቲው የደንበኞችን መረጃ ደህንነት ባለመጠበቅ ቅጣት የተላለፈበት የመጀመሪያው ነው ተብሏል።

ዩኒቨርሲቲው ክሱን ያልተቃወመ ሲሆን፥ የተወሰነበት የገንዘብ ቅጣት ከ120 ሺህ ወደ 96 ሺህ ዩሮ ዝቅ እንዲልለት አቤቱታ ማቅረቡ ነው የተገለጸው።

 

 

 

 

 

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ

 የተተረጎመና የተጫነው፦ በእንቻለው ታደሰ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *