የፌስቡክን መረጃ በመበርበር የተከሰሰው ካንብሪጅ አናላቲካ በኤፍ ቢ አይ እየተመረመረ ነው

Home of best apps

የፌስቡክን መረጃ በመበርበር የተከሰሰው ካንብሪጅ አናላቲካ በኤፍ ቢ አይ እየተመረመረ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ87 ሚሊየን ሰዎችን የግል መረጃ በመበርበር የተከሰሰው ካንብሪጅ አናላቲካ በአሜሪካ ፍትህ መምሪያ እና ኤፍ ቢ አይ ምርመራ እንደተጀመረበት ተገለፀ።

የካንብሪጅ ሰራተኞች ፣ በጋራ የሚሰሩ ባንኮች እና ሌሎች ከተቋሙ ጋር ግንኙነት ያላቸው አካላት በመርማሪዎች ጥያቄ እንደሚቀርብላቸው ነው የተነገረው።

ካንብሪጅ አናላቲካ የበርካቶችን መረጃ እንደበረበረ መረጃዎች ከተለቀቁ በኋላ ደንበኛን በማጣቱ ምክንያት በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ መዘጋቱ ይታወሳል።

በአሜሪካ በፈረንጆቹ 2016 በተካሄደው ምርጫ ለዶናልድ ትራምፕ ምርጫ ቅስቀሳ በአማካሪነት የተሳተፈው ተቋሙ በወቅቱ የ87 ሚሊየን ሰዎችን የግል መረጃ ያለአግባብ እንደተጠቀመ ክስ የቀረበበት ሲሆን፥ በአሜሪካ እና አውሮፓ በርካታ ምርመራዎች እንደተካሄዱበት ተነግሯል። 

የአሜሪካ ፍትህ መምሪያ እና ኤፍ ቢ አይ በተቋሙ ገንዘብ ነክ ጉዳዮች፣ የበረበራቸውን መረጃዎች ከፌስቡክ እና ከሌሎች ምንጮች በምን አይነት መልኩ እንዳገኛቸው እና እንደተጠቀማቸው በሚያሳዩ ጉዳዮች ላይ ምርመራው እንደሚደረግበት ታውቋል።

ንዲሁም በካንብሪጅ አናላቲካ ላይ ምርመራ እያደረጉ የሚገኙት አካላት ከፌስቡክ አመራሮች ጋር መገናኘታቸው ተነግሯል።

ሆኖም ምርመራውን የሚመሩት የአሜሪካ ፍትህ መምሪያ፣ ኤፍ ቢ አይ አና ፌስቡክ በጉዳዮ ዙሪያ አስተያየታቸውን ለመስጠት መቆጠባቸው ተገልጿል።

ምንጭ፦ሮውይተርስ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *