ካርስፐርስክይ ኩባንያ የመረጃ ቋቱን ከሩሲያ ሊያወጣ ነው

Home of best apps

ካርስፐርስክይ ኩባንያ የመረጃ ቋቱን ከሩሲያ ሊያወጣ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት07፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት ጊዚያት በመረጃ ደህንነት ጉዳይ ከአሜሪካ መንግስት ውንጀላዎች ሲቀርቡበት የቆየው ካርስፐርስክይ ኩባንያ የመረጃ ቋቱን ከሩሲያ ሊያወጣ መሆኑ ተገልጿል።

የሩሲያ የደህነነት ሰዎች የካርስፐርከይ ቴክኖሎጂ ውጤቶቶችን በመጠቀም ተፈለጊ የሆኑ የአሜሪካ መረጃዎችን ለመበርበር ጥቅም ላይ አውለዋል በሚል ውንጀላ እየቀረበበት ያለው ይህ ኩባንያ በርካታ ዓለም አቀፍ ደንበኞች ያሉት ሲሆን የእነዚህ ደንበኞች ታማዓኒነት ለማረጋገጥ ሲል የመረጃ ቋቱን ለማዛውር የወሰነ መሆኑ ነው የተገለጸው።

የመራጃ ማስቀመጥ፣ ሶፍትዌሮችን የማላመድና የመረጃ መረብ ደህንነት ላይ የሚሰራው  ካርስፐርስክይ ኩባንያ  ሰሜን አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ ሲንጋፓር፣ አውስትራለያ፣ ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ  ደንበኖቹ መሆናቸውን ነው መረጃው የሚያመላክተው።

በፈረንጆቹ 2019 ማብቂያ ላይም ኩባንያው በዙሪክ የተሟለ አገልግሎቱን ይሰጣልም ተብሏል።

የመረጃ መረብ ደህንነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ባአለበት በአሁኑ ሰዓት ኩባንያው ለደንበኞቹ ግልጽነትና ታማኝነት በተሟላበት መንገድ አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ እንደሆነ ነው የተገለጸው።

 

 

 

 

 

 

 

ምንጭ፦ axios.com

 

የተተረጎመና የተጫነው በእንቻለው ታደሰ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *