ፌስቡክ የደንበኞቼን መረጃ ያለአግባብ ሲጠቀሙ ነበር ያላቸውን 200 መተግበሪያዎች አገደ

Home of best apps

ፌስቡክ የደንበኞቼን መረጃ ያለአግባብ ሲጠቀሙ ነበር ያላቸውን 200 መተግበሪያዎች አገደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፌስቡክ የደንበኞቼን መረጃ ያለአግባብ ሲጠቀሙ ነበር ያላቸውን 200 መተግበሪያዎች ማገዱን አስታወቀ።

ፌስቡክ መተግበሪያዎችን አግዷል የሚለው አሃዝ የወጣው ካንብሪጅ አናላይቲካ የተባለው ኩባንያ የግለሰቦችን መረጃ አለአግባብ መጠቀሙን ተከትሎ በሀሉም መተግበሪያዎች ላይ ባካሄደው ኦዲት ነው ተብሏል።

ማጣሪያ የተደረገባቸው መተግበሪያዎች ከፌስቡክ ጋር ሲሰሩ የነበሩ መሆናቸውም ተነግሯል።

ፌስቡክ መተግበሪያዎቹ ላይ በሁለት መልኩ ማጣሪያ ካካሄደ በኋላ የግለሰቦችን መረጃ ያለአግባብ ተጠቅመዋል ያላቸውን 200 መተግበሪያዎቹን ያገደው ተብሏል።

በያዝነው ዓመት ከፌስቡክ ጋር ሲሰራ የነበረው ካንብሪጅ አናሊኪካ የተባለ ተቋም የ87 ሚሊየን የፌስቡክ ተጠቃሚዎችን መረጃ ያለ አግባብ ተጠቅሟል የሚለው መረጃ ይፋ መውጣቱ ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎም ፌስቡክ የግለሰቦችን መረጃ ያለአግባብ የሚጠቀሙትን እንደሚያግድ እና ለተጠቃሚዎችም መረጃቸው አላግባብ መመዝበሩን የሚያሳይ ማሳወቂያ እልክላቸዋለሁ ማለቱ ይታወሳል።

በተጨማሪም የኩባንያው መስራች ማርክ ዙከርበርግ “ክሊር ሂስትሪ” የተባለ አዲስ ቁልፍ ያስተዋወቀ ሲሆን፥ ይህም መተግበሪያዎች መረጃዎችን እንዳይሰበስቡ የተጠቀምናቸውን በሙሉ ለማጥፋት የሚረዳ ነው።

ምንጭ፦ www.huffingtonpost.co.uk

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *