ጎግል ኩባንያ በምርጫ ቅስቀሳ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ አዲስ አሰራር ሊያቀርብ ነው

Home of best apps

ጎግል ኩባንያ በምርጫ ቅስቀሳ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ አዲስ አሰራር ሊያቀርብ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ፣ 30፣ 2010፣ (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጎግል ኩባንያ በሚቀጥለው የአሜሪካ ምርጫ ተሳታፊዎች የአሜሪካ ነዋሪዎች ወይንም ዜጎች መሆናቸውን ለመለየት የሚያስችለውን አሰራር ተግባራዊ የማድረግ ፍላጎት እንዳለው ገልጿል።

ኩባንያው የምርጫ ተሳታፊዎችን ማንነት ማረጋገጥ መቻሉ አሰራሩን ለመሻሻልና ግልጽ የምርጫ ቅስቀሳ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችለውም ነው የተገለጸው።

የኩባንያው ምክትል ስራ አስኪያጅ ኬንት ዋልከር እንደተናገሩት ኩባንያው በአሰራሩ ላይ ለውጥ ማድረጉ ለደንበኞቹ ታማኒ አገልግሎት ከመስጠት በተጨማሪ የምርጫ ቅስቀሳ ማስታዎቂያ ለማሰራት ፍላጎት ላላቸው አካላት አገልግሎቱን በግልጽ ለመስጠት ያስችለዋል።

ይሁን እንጂ የምርጫ ቅስቀሳ ማስታዎቂያዎችን ለማሰራት ወደ ኩባንያው የሚመጡ አከላት በዘርፉ ፈቃድ ያላቸው ለመሆኑ ከመንግስት የተሰጣቸው የመታዎቂያ ካርድና ሌሎች መሰረታዊ መረጃዎችን ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸው ነው የተናገሩት።

ኩባንያው የዘርፉን አገልገሎት ለደንበኞቹ ለመስጠት በአሜሪካው ምርጫ የመታወቂያ ካርድ መጠየቅ የመጀመር ሀሳብ ያለው ሲሆን፥ ይህንኑ አሰራር በሌሎች ምርጫዎችና የምርጫ ሂደቶች ላይ የማስፋፋት ፍላጎት እንዳለው ነው የተመላከተው።

እንደ ምክትል ስራ አስኪያጁ ገለፃ ኩባንያው የምርጫ ቅስቀሳ ማስታዎቂያ አገልግለሎቶችን ለመስጠት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችንና ክፍያ የተመለከተ ዝርዝር መረጃዎችን በሚቀጥሉት ጊዚያት ይፋ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

በአዲሱ የኩባንያው የምርጫ ቅስቀሳ ማስድታዎቂያ አሰራር መሰረት የማስታወቂያ ባለቤቶችን ማንነት በግልጽ እንደሚቀመጥ ነው ዘገባው የሚያስረዳው።

የማህበራዊ ሚዲያ ኩባንያዎች በቀላሉ ለመረጃ በርባሪዎች እየተጋለጡ በመሆናቸው ፌስቡክና ቲዊተር የምርጫ ቅስቀሳ ማስታዎቂያ አገልግሎት አሰጣጣቸው ላይ ማስተከከያ እያደረጉ መሆናቸውንም ዘገባው አስታውሷል።

 

 

 

 

 

ምንጭ፦ bbc.com

 

የተተረጎመና የተጫነው፦ በእንቻለው ታደሰ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *