ኬንያ የመጀመሪያዋን ሳተለይት ልታመጥቅ ነው

Home of best apps

ኬንያ የመጀመሪያዋን ሳተለይት ልታመጥቅ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ፣29፣2010፣ (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኬንያ የመጀመሪያውን ሳተለይቷት በሚቀጥለው አርብ ለማምጠቅ በዝግጅት ላይ መሆኗ ተገለጸ።

ሳተለይቷን የማምጠቅ ስነ ስርዓቱም በፈረንጆቹ አቆጣጠር ግንቦት 11 2018 በጃፓን ኪቦ የሳተላይት ሙከራ ማዕከል እንደሚከናዎንም ነው የተገለጸው።

መንኮራኩሯ ኪቦ ከተባለው የጃፓን የጠፈር ምርምር ማዕከል እንደምትመጥቅም ነው መረጃዎች የሚያመላክቱት።

የኬንያ ዩንቨርሲቲ ተመራማሪዎች፣ ተማሪዎችና የጃፓን የጠፈር ተመራማሪወች ከባለፈው ጥር ወር ጀምሮ ለዚሁ ፕሮግራም መሳካት በጋራ ሲሰሩ እንደቆዩም ዘገባው አመላክቷል።

የናይሮቢ ዩንቨርሲቲ የውጭ ግንኙነት ዳይሬክተር ጆን ኦሪዲኒ እንደገለጹትም በሀገሪቷ የትምህርት ካቢኒዋ ዋና ጸሃፊ አምባሳደደር አሚና ሙሀመድ የሚመራ ቡድን ፕሮግራሙን ለመከታተል ወደ ጃፓን ያቀናል።

የሳተላይት ማምጠቅ ስነስርዓቱን በቦታው ተገኝቶ በቀጥታ የሚከታተለው ሉዑክ ከሀገሪቱ ዩንቨርሲቲ የተውጣጡ ተመራማሪዎችና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትናን እንደሚካትት ነው ዘገባው የሚያመላክተው።

አጠቃላይ ፕሮግራሙን በተመለከተ በነገው ዕለት በምስልና ድምጽ የታገዘ ተጨማሪ ማብራሪ ከቦታው ይለቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም ታውቋል።

 

 

 

 

 

 

ምንጭ፦ nation.co.ke

የተተረጎመና የተጫነው ፦ በእንቻለው ታደሰ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *