ሮቦቶች ምግብ የሚያበስሉበት ሬስቶራንት

Home of best apps

ሮቦቶች ምግብ የሚያበስሉበት ሬስቶራንት

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 29፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሜሪካዋ ቦስተን ከተማ የሚገኝ የአንድ ሬስቶራት የምግብ ማብሰያ ክፍል ሙሉ በሙሉ በሮቦቶች የሚመራ መሆኑ ተነገረ።

በኤም.አይ.ቲ ምሩቃን ተሰሩ የተባሉት ሮቦቶቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ የታዘዙትን ምግብ አብስለው የሚያቀርቡልን መሆኑ ነው የተነገረው።

ሮቦቶቹ የታዘዙትን የምግብ አይነቶች በሶስት ደቂቃ ውስጥ ያቀርባሉ የተባለ ሲሆን፥ ተገልጋዮች ለአንድ ምግብ 7 ዶላር ገደማ ይከፍላሉ ነው የተባለው።

ተገልጋዮች እንዲመጣላቸው የሚፈልጉትን የምግብ አይነትም በተች ስክሪን አማካኝነት ነው የሚያዙት ተብሏል።

ሆኖም ግን ሮቦቶቹ ሁሉንም ስራ በራሳቸው አይደለም የሚሰሩት የተባለ ሲሆን፥ ምግቡን ለመስራት የሚያስፈልገውን ቅድመ ዝግጅቶችና ከተጠናቀቀ በኋላ ይዘው ለሚሄዱት የመጠቅለሉን ስራ ሰዎች ናቸው የሚሰሩት።

ሮቦቶቹ ከሬስቶራንቶቹ በተጨማሪም ቤት ውስጥ ቤተሰብ በዝቶባቸው ብቻቸውን ምግብ ለማዘጋጀት ለሚቸገሩ ሰዎችም ስራን ያቀላሉ በሚል ተስፋ ተጥሎባቸዋል።

ምንጭ፦ www.huffingtonpost.co.uk

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *