ቲዊተር 330 ሚሊየን ደንበኞቹ የይለፍ ቁልፎቻቸውን እንዲቀየሩ አሳሰበ

Home of best apps

ቲዊተር 330 ሚሊየን ደንበኞቹ የይለፍ ቁልፎቻቸውን እንዲቀየሩ አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ፣26፣(ኤፍ.ቢ.ሲ) ቲዊተር 330 ሚሊየን ደንበኖቹ የይለፍ ቁልፎቻቸውን መቀየር እንዳለባቸው ያስጠነቀቀው የውስጥ አሰራሮቹ ላይ ችግሮች እንደገጠሙት ካረጋገጠ በኋላ ነው ተብሏል።

የማህበራዊ ድረገጹ የደንበኞቹ የይለፍ ቁልፎች በሌሎች ሰዎች አገልግሎት ላይ ይዋሉ አይዋሉ ለማረጋገጥ እንዳልቻለም ነው የተገለጸው። 

 ኩባንያው ከጥቂት ሳምንታት በፊት ችግሩ እንደተከሰተ ያረጋገጠ ሲሆን፥ የተከሰቱ ጉድለቶችን እንዲያርሙ ለኩባንያው ሰራተኞች ሪፖርት ማድረጉም ታውቋል።

 በዚህም ደንበኞቹ የይለፍ ቁልፎቻቸውን በመቀየር ኩባንያው ለደንበኞች የመረጃ ደህንነት ጥበቃ ለሚያደርገው ጥንቃቄ እገዛ ማድረግ እንዳለባቸው ጥሪውን አስተላልፏል ተብሏል።

 ይሁን እንጂ ኩባንያው የምን ያህል ደንበኞቹ የይለፍ ቁልፎች ላይ ጥቃቱ እንደተፈጸመ መረጃ እንዳልሰጠም ዘገባው ያመላክታል።

 

 

 

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ

 

የተተረጎመና የተጫነው፦ በእንቻለው ታደሰ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *