ተመራማሪዎች ያለገደብ መልሶ ጥቅም ላይ የሚውል አዲስ ፕላስቲክ ሰሩ

Home of best apps

ተመራማሪዎች ያለገደብ መልሶ ጥቅም ላይ የሚውል አዲስ ፕላስቲክ ሰሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 22፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተመራማሪዎች ቡድን በአይነቱ አዲስ የሆነ ፕላስቲክ መስራታቸው ተነግሯል።

የኮለራዶ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች የሰሩት አዲሱ ፕላስቲክ በመልሶ ጥቅም ላይ ማዋል ዘዴ ያለ ገደብ በድግግሞሽ በማምረት ለመጠቀም የሚያስችል ነው።

በዩኒቨርሲቲው የኬሚስትሪ ትምህርት ክፍል ፕሮፌሰር ኢዩጂን ቼን እንደሚናገሩት፥ አዲሱ ግኝት በየዓመቱ የምንጥለውን የፕላስቲክ ቆሻሻ መጠን ለመቀነስ አይነተኛ መፍትሄ ነው ብለዋል።

በየዓመቱ 12 ሚሊየን ቶን የፕላስቲክ ቆሻሻዎች በውቂያኖሶች ላይ አንደሚጣሉም መረጃዎች ያመለክታሉ።

ከዚህ ቀደም የሚጣሉ ፕላስቲኮችን በመልሶ ጥቅም ላይ የማዋል ዘዴ ዳግም ለሌላ አገልግሎት እንዲውሉ ቢደረግም፤ የጥራታቸው መጠን እየቀነሰ ሄዶ መጣላቸው ስለማይቀር አካባቢን መበከሉ የማይቀር ነበር።

ይህ ጉዳይ ነው በፕሮፌሰር ቼን የተመራው የተመራማሪዎች ቡድን አዲስ ፕላስቲክ አንዲሰራ ያነሳሳው።

በዚህም “ፖሊመር” የሚል ፕላስቲክ መስራታቸውን ያስታወቁት ተመራማሪዎቹ፥ አንድ ጊዜ ከተጠቀምነው በኋላ ጥራቱ ሳይጓደል በመልሶ ጥቅም ላይ ማዋል ዘዴ ያለገደብ ለመተመሳሳይ አገልግሎት መጠቀም እንችላለን።

“ፖሊመር” ገና ወደ ምርት ሂደት ለመግባት የመጀመሪያ ደረጃ ላይ ሲሆን፥ የተመራማሪዎች ቡድን ግን ግኝቱ በቶሎ ወደ ምርት ሂደት እንዲገባና ውጤታማነቱን ለማየት በፍጥነት እየሰሩበት መሆኑ ተነግሯል።

ምንጭ፦ www.huffingtonpost.co.uk

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *