የመረጃ መረብ ጠላፊዎች በሚሊየን የሚቆጠሩ የሆቴል ክፍሎችን የሚከፍት ቁልፍ መስራታቸው ተነገረ

Home of best apps

የመረጃ መረብ ጠላፊዎች በሚሊየን የሚቆጠሩ የሆቴል ክፍሎችን የሚከፍት ቁልፍ መስራታቸው ተነገረ

አዲስ አበባ ሚያዚያ፣ 22፣ 2010፣(ኤፍ.ቢ.ሲ) የመረጃ መረብ ጠላፊዎች ያለ አንዳች አሻራ በደቂቃዎች የዓለም ዓቀፍ ሆቴሎች ክፍሎችን በር ለመክፈት የሚያስችል ቁልፍ (ማስተር ኪ) መስራታቸውን የሳይበር ጥቃት ደህንነት ተመራማሪዎች ገለፁ።

በፊንላንድ የመረጃ መረብ ደህንነት ኩባንያ የዘረፉ አማካሪ የሆኑት ቶሚ ቱሚኔንና ቲሞ ሂርቮኔን እንደገለፁት “ቪንግ ካርድ ኤልሴፍ” የተባለ ዘመናዊ የሆቴሎች የኤሌክትሮኒክስ ቁልፎች ላይ ሶፍትዌር ላይ ጥቃት መፈጸሙ ተረጋግጧል።

ኣሳ አብሎይ የተባለው ኩባንያ ምርት የሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ቁልፎቹ በማእከል ላይ ለሚገኘው የኩባንያው ሰርቨር ምላሽ ያለመስጠታቸውንም ተናግረዋል።

በዚህም በዓለም አቀፍ ደረጃ በሆቴሎች ላይ የተከሰተውን ችግር ለመቅረፍ ረዘም ያለ ጊዜ የሚወስድ መሆኑንም ነው የገለጹት።

የዚህ ሶፍትዌር ጥቃት በ166 ሀገራት በሚገኙ ወደ 40 ሺህ ለሚጠጉ ህንፃዎች ስጋት መሆኑንም ነው መረጃው የሚያመላክተው።

ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ ቁልፍ ሶፍትዌሮችም በዚሁ የመረጃ በርባሪዎች ቁልፍ ጥቃት ሊደረስባቸው እንደሚችል ስጋት ያላቸው መሆኑን ተመራማሪዎቹ ገልፀዋል።

የኩባንያው ቃል አቀባይ ችግሩን አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ፥ አሳ አብሎይ ችግሮቹን ለመቅረፍና ጥራትና ብቃት ያለው አገልግሎት ለደንበኞቹ ለመስጠት እየሰራ መሆኑን አመላክተዋል።

ተመራማሪዎቹ በጉዳዩ ላይ የደረሱበትን አዲስ ውጤት በሚቀጥለው ሳምንት መጨረሻ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ነው በዘገባው የተገለጸው።

የኣሳ አብሎይ የኤሌክትሮንክስ ሶፍት ዌር ቁልፎችን ለረጅም ዓመታት ከሚጠቀሙ ዓለም አቀፍ ሆቴሎች መካከልም ሀያት፣ ራዲሰንና ሸራተን ተጠቅሰዋል።

 

 

 

 

 

 

ምንጭ፦ techworm.net

 

 

የተተረጎመና የተጫነው፦ እንቻለው ታደሰ

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *