ፌስ ቡክ የካምብሪጅ አናሊቲካ ማስጠንቀቂያ ለተጠቃሚዎች እየላከ ነው

Home of best apps

ፌስ ቡክ የካምብሪጅ አናሊቲካ ማስጠንቀቂያ ለተጠቃሚዎች እየላከ ነው

አዲስ አበባ ሚያዚያ 2፣ 2010፣ (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፌስቡክ የደንበኞች መረጃ በካምብሪጅ አናሊቲካ መበርበር አለመበርበሩን ማረጋገጥ የሚያስችል መልዕክት ለተጠቃሚዎች እየላከ ነው።

ኩባንያው ለሁሉም የገጹ ተጠቃሚዎች ሁለት የተለያዩ መልዕክቶችን እያደረሰ ሲሆን፥ ደንበኛውም የፌስ ቡክ አድራሻው በተባለው ተቋም መበርበር አለመበርበሩን እንዲያውቅ ያስችለዋል።

 ተጠቃሚዎቹ መልዕክቱ ሲደርሳቸው መረጃውን ለመበርበር ጥቅም ላይ የዋለው መተግበሪያ እና መተግበሪዎቹ ሊይዙ የሚችሉትን መረጃ ምን ሊሆን እንደሚችል የማወቅ እድል ይኖራቸዋልም ተብሏል።

የፌስ ቡክ ደንበኞቹ በተላከላቸው መልዕክት አማካኝነትም የፌስ ቡክ አድራሻቸው ከተበረበረባቸው 87 ሚሊየን ተጠቃሚዎች አንዱ መሆን አለመሆናቸውን ያውቃሉ ነው የተባለው።

ኩባንያው አሁን ላይ ከደረሰው የመረጃ ብርበራ ጋር በተያያዘ፥ ኩቤዩ የተባለውን የተጠቃሚዎችን አድራሻና ማንነት የተመለከቱ ትንታኔዎችን የሚሰራ ተቋምን ማገዱም ተሰምቷል።

ፌስ ቡክ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ኩቤዩ መረጃዎችን የሰበሰበው ለጥናትና ምርምር ይሁን አይሁን ማወቅ ስላልቻልኩ ነው ብሏል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ተቋሙ የሰበሰባቸው መረጃዎች ለምን ግልጋሎት እንዳዋላቸው ሳያረጋግጥ ከተቋሙ ጋር አብሮ የመስራት ፍላጎት እንደሌለውም ገልጿል።

አሁን ላይም ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ተቋሙ የሰበሰባቸውን መረጃዎች ለጥናትና ምርምር ወይስ ለሌላ አገልግሎት እየተጠቀመባቸው መሆን አለመሆኑን፥ የብሪታኒያውን ካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ጨምሮ ምርመራ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።

ይሁን እንጂ ኩቤዩና ካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የተጠቃሚዎችን አጠቃላይ መረጃ ለመተንተን የተጠቀሙትን መተግበሪያ ለጥናትና ምርምርና ለቢዝነስ ስራ ብቻ እንደተጠቀሙበት ገልጸዋል።

ወደብሉምበርግ የተላከ አንድ የኢሜል መልዕክት ደግሞ ኩቤዩ ጉዳዩን በትክክል የማያስረዳ ከሆነ መተግበሪያዎቹ ከፌስ ቡክ ሙሉ በሙሉ እንደሚሰረዙ ያስረዳል።

ተቋሙ በበኩሉ በፌስቡክ የአገልግለት መመሪያ መሰረት እንደሚጠቀምና ህጎችን እንደሚያከብር አስረድቷል።

ኩቤዩ የደንበኞችን ስም፣ ፍላጎት፣ ስሜት እንዲሁም ጠቅለል ያሉ መረጃዎችን በመተንተን አገልግሎት የሚሰጥ መተግበሪያ ነው።

ባለፈው ደርሷል ከተባለው የ87 ሚሊየን የፌስ ቡክ ተጠቃሚዎች መረጃ ብርበራ ጋር በተያያዘ ያሉ ጉዳዮችን፥ የኩባንያው መስራችና ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ ከዛሬ ጀምሮ ማስረዳት ይጀምራል።

 

 

 

 

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ

 

የተተረጎመና የተጫነው ፦ እንቻለው ታደሰ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *