ከዋትስአፕ ጋር ተመሳስሎ የተሰራ ሀሰተኛ መተግበሪያ የሰዎችን የግል መረጃ እየዘረፈ ነው ተባለ

Home of best apps

ከዋትስአፕ ጋር ተመሳስሎ የተሰራ ሀሰተኛ መተግበሪያ የሰዎችን የግል መረጃ እየዘረፈ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከዋትስአፕ መተግበሪያ ጋር ተመሳስሎ የተሰራ የሀሰት መተግበሪያ የግለሰቦችን መረጃ ለመዝረፍ ጥቅም ላይ እየዋለ መሆኑ ተነግሯል።

“ዋትስአፕ ፕላስ (WhatsApp Plus)” የሚል መጠሪያ የተሰጠው አዲሱ ሀሰተኛ መተግበሪያ በአሁኑ ወቅት በስፋት ኢንተርኔት ላይ የተለቀቀ መሆኑንም የአሜሪካ የኢንተርኔት ደህነንት ኩባንያ የሆነው ማልዌርባትስ የምርምር ማእከል አስታውቋል።

እንደ ኩባንያው ገለፃ ሀሰተኛ መተግበሪያው ተጨማሪ የዋትስአፕ አገልግሎቶችን ለመስጠት የቀረበ መስሎ የተሰራ ቢሆንም፤ የሰዎችን ግላዊ መረጃ ለመዝረፍ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ ነው።

ሀሰተኛ መተግበሪያው ከስማርት ስልካችን ላይ ጭምር ፎቶ ግራፎችን፣ የስልክ ቁጥሮችን እና የተለያዩ የግል መረጃዎቻችነን በመዝረፍ በቫይረስ የሚተካ መሆኑንም ኩባንያው አስታውቋል።

መተግበሪያ በጎግል ፕላስም ይሁን በአፕል ስቶር ላይ ያልቀረበ ቢሆንም፤ በብሎግ ፖስት የአስተያየት መስጫ ሳጥኖች ውስጥ እና በተለያዩ መንገዶች ኢንተርኔት ላይ እየተሰራጨ ይገኛል።

መተግበሪያውን አንድ ጊዜ ከጫንን በኋላም ወዲያውኑ በስልካችን ላይ የያዝነውን የግል መረጃዎቻችንን መዝረፍ እንደሚጀምር ነው ኩባንያው ያስታወቀው።

ሀሰተኛውን መተግበሪያ በስህተት ጭነን አንደሆነም በአፋጣኝ ማጥፋት ይገባል ሲሉም የኩባንያው ተመራማሪዎች ምክራቸውን ለግሰዋል።

ምንጭ፦ www.techworm.net

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *