አፕል ያለ እጅ ንኪኪ ትእዛዝ የሚቀበል ስልክን ይፋ ሊያደርግ ነው

Home of best apps

አፕል ያለ እጅ ንኪኪ ትእዛዝ የሚቀበል ስልክን ይፋ ሊያደርግ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አፕል ኩባንያ የስልክ ስክሪን መስታወት ሳይነካ የሚፈለገውን አገልግሎት መስጠት የሚችል ስልክን ይፋ ሊያደርግ መሆኑ ተነገረ።

ይህ ከላይ ወደ ታች የታጠፈ ስክሪን የሚኖረው ስልክ አፕልን በዘርፉ ተወዳዳሪ እንደሚደርግ ይጠበቃል።

ይህ የአፕል ፈጠራ የስልኩን ስክሪን ሳይነኩ የእጅ ጣትዎን ወደ ስልኩ ብቻ በማቅረብ ስልኩን መጠቀም ያስችላል ተብሏል።

ከዚህ በፊት ስክሪናቸው ጠርዝ ላይ እጥፍ ያለ ስልኮች በሳምሰንግ ኩባንያ በኩል ተዘጋጀቶ እንደነበር ያስታወሰው መረጃው ይህ የአፕል ፈጠራ ግን የተለየ ነገር ይዞ እንደመጣ ነው የተገለፀው።

ስክሪኑ የሚታጠፈው የሳምሰንግ ስልክ ውስንነቶች እንዳሉበት የተነገረ ሲሆን፥ አፕሉ ግን ከላይ እሰከ ታች ድረስ ስክሪኑ ቀስ እያለ እየታጠፈ የሚሄድ ነው።

ስክሪኑ በምልክት የሚሰራው ይህ ስልክ አሁን የማሳደግ ስራ እየተከናወነለት ሲሆን፥ በመጪዎቹ ሁለት እና ሶስት አመታት ገበያ ላይ እንደሚውልም ተነግሯል።

ምንጭ፦ ፎስባይት

ተተርጉሞ የተጫነው፦ በኤፍሬም ምትኩ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *