ኢትዮጵያ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን የዲጂታል የንግድ ምልክት ማሳወቂያ ድረገጽ ስራ አስጀመረች

Home of best apps

ኢትዮጵያ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን የዲጂታል የንግድ ምልክት ማሳወቂያ ድረገጽ ስራ አስጀመረች

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 27፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢፌዴሪ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽህፈት ቤት ቤት ዲጂታል የንግድ ምልክት ማሳወቂያ ድረገጽን አስመርቀ።

ድረገጹ በድርጅቶች የተመዘገቡ የንግድ ምልክቶችን ለማሳወቅ የሚረዳ ሲሆን፥ ከዓለም የአዕምሮዊ ንብረት ድርጅት ጋር በመተባበር የተሰራ ነዉ ተብሏል።

ድረገፁን መርቀው ስራ ያስጀመሩት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢኒጂነር ጌታሁን መኩሪያ የንግድ ምልክት ማሳወቂያ ድረገጽ በአፍሪካ የመጀመርያዉ መሆኑንም መግለፃቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

ያለፉት ሁለት ዓመታት መረጃ እንደሚያሳየዉ ከሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ 4 ሺህ 190 የንግድ ምልክቶች በዓለም አቀፉ አዕምሯዊ ንብረት ድርጅት ተመዝግበዋል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *