በፊስቡክ ላይ መረጃዎቻቸው የተበረበረባቸው ተጠቃሚዎች 87 ሚሊየን ደርሷል

Home of best apps

በፊስቡክ ላይ መረጃዎቻቸው የተበረበረባቸው ተጠቃሚዎች 87 ሚሊየን ደርሷል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣2010 (ኤፍ. ቢ. ሲ) በካንብሪጅ አናላቲካ የፈስቡክ መረጃዎቻው የተበረበረባቸው ተጠቃሚዎች ቁጥር 87 ሚሊየን መድረሱን ፊስቡክ ይፋ አደረገ።

ከዚህ በፊት የፈስቡክ መረጃቸው የተበረበረባቸው ተጠቃሚዎች ቁጥር 50 ሚሊየን እንደሆነ መነገሩ ይታወሳል።

የግለሰቦች መረጃ እንዲበረበር የሚያስችለውን መተግበሪያ የሚጠቀሙት 270 ሺህ እንደሆኑ ቢነገርም ተጠቃሚዎቹ 305 ሺህ ናቸው ተብሏል።

ይህን መተግበሪያ ከሚጠቀሙት 97 በመቶዎቹ አሜሪካውያን ሲሆኑ 16 ሚሊየን የሚጠጉት ደግሞ የሌሎች ሀገራት ተጠቃሚዎች እንደሆኑ ተጠቁሟል።

የፊስቡክ መስራችና ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት በርካታ ስራዎች እንደተከናወኑ ገልጿል በቀጣይም ችግሩን ለመቅረፍ እንደሚሰራ ነው የገለፀው።

የውስጥ አሰራርን በጊዜ አለመፈተሽ እና መረጃ መንታፊዎች ተጠቃሚዎች የግለሰቦችን ኢሜይል ወይንም ስልክ ቁጥር በመጠቀም ማግኘት እንዲችሉ ማድረጋቸው ለዚህ ችግር መፈጠር በምክንያትነት ተጠቅሷል።

ካንብሪጅ አናላቲካ የተበረበሩትን መረጃዎች ማጥፋቱን የገለፀ ሲሆን በጉዳዩ ዙሪያ ምርመራ ያደረጉ ሚዲያዎች ግን የተወሰኑ ግለሰቦች መረጃ አሁንም በተቋሙ የመረጃ ቋት ውስጥ እንሚገኝ አስታውቀዋል።

እንዲሁም ተቋሙ የ87 ሚሊየን ሳይሆን የ30 ሚሊየን ተጠሚዎችን መረጃዎች አግኝቶ እንደነበረ ነው ያስታወቀው።

ፊስቡክን በተሻለ መንገድና ጥንቃቄ ለመጠቀም የሚያስችሉ መተግበሪያዎችን በቀጣይነት ሲያዘጋጅ ጥናቃቄ እንደሚወስድ ያስታወቀው ተቋሙ፥ ሌሎች የአሰራር ስርዓቶችን እየዘረጋ እንደሆነም ይፋ አደርጓል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ተተርጉሞ የተጫነው፦ በኤፍሬም ምትኩ