በቻይና የኮንትሮባንድ ነጋዴዎች ድሮን በመጠቀም የሞባይል ስልኮችን ከሆንግ ኮንግ እያስገቡ ነው

Home of best apps

በቻይና የኮንትሮባንድ ነጋዴዎች ድሮን በመጠቀም የሞባይል ስልኮችን ከሆንግ ኮንግ እያስገቡ ነው

አዲስ አበባ መጋቢት ፣21 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቻይና የሚገኙ የኮንትሮባንድ ነጋዴዎች ድሮኖችን በመጠቀም በህገወጥ መንገድ የሞባይል ስልኮችን ከሆንግ ኮንግ በማስገባት ላይ መሆናቸው ተነገረ።

የኮንትሮባንድ ነጋዴዎቹ 78 ነጥብ 8 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የሚገመት ዘመናዊ ስልኮችን ከሆንግ ኮንግ ወደ ሸንዜን በመጠቀም ማስገባታቸው ነው የተገለፀው።

 

ሀገሪቱ በዚህም የተጠረጠሩ 26 ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውላለች።

በቻይና ድሮን በመጠቀም ወንጀል ሲፈፀም ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሆነ ነው የተገለፀው።

የኮንትሮባንድ ነጋዴዎቹ በአንድ ምሽት ብቻ እስከ 15 ሺህ ስልኮችን በዚህ መንገድ ወደ ሸንዜን አስገብተዋል።

በቻይና እነዚህን ሰው አልባ በራሪዎችን (ድሮን) አጠቃቀምን ስርዓት ማስያዝ ዋና ተግባራ እንደሚሆን መንግስት ገልጿል።

እንዲሁም ቻይና ድሮን የአውሮፕላን በረራን እንዳያስተጓጉሉ በባለፈው አመት ህግ ማውጣቷ የተነገረ ሲሆን፥ ተጠቃሚዎች የሚይዙት የእቃ አይነትም ማስመስዝገብ ይጠበቅባቸዋል።

ምንጭ፦ ሮውይተርስ