ቴስላ 123 ሺህ መኪናዎቹን ጠራ

Home of best apps

ቴስላ 123 ሺህ መኪናዎቹን ጠራ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መቀመጫውን በዩናይትድ ስቴትስ ያደረገው ቴስላ የቴክኖሎጂ ኩባንያ በቴክኒክ ችግር ምክንያት 123 ሺህ መኪኖችን መጥራቱን አስታወቀ።

የተጠሩት መኪኖች በአውሮፓውያን ከ2016 በፊት የተመረቱ ናቸው ተብሏል።

የቴስላ ቃልአቀባይ መኪኖቹ ሊጠሩ የቻሉት ከዝገት ጋር በተገናኘ መሆኑን ገልፀዋል።

እስካአሁን በተጠቀሰው ችግር አደጋ ያደረሰ መኪና የለም ተብሏል።

ድርጅቱ ለሁሉም የመኪናው ተጠቃሚዎች ኢሜይል መላኩን ነው ያስታወቀው።

ሆኖም ዜናው ከተሰራጨ ጀምሮ የድርጅቱ አክስዮን ገበያ በ4 በመቶ መቀነሱ ተነግሯል።

ቴስላ ከዚህ ቀደም በቴክኒክ ችግር ምክንያት መኪኖቹን ሲጠራ የመጀመሪያው አይደለም።

ባለፈው ዓመት 53 ሺህ መኪኖችን የጠራ ሲሆን፥ በዚያው ዓመት ከአንድ ወር ቆይታ በኋላ 11 ሺህ መኪኖችን መጥራቱ የሚታወስ ነው።

 

 

 

ምንጭ፦ሲኤንኤን
ተተርጉሞ የተጫነው፦ በአብረሃም ፈቀደ