ቻይና ፊት በማየት ብቻ መላ ህዝቧን በአንድ ሰከንድ ውስጥ ማንነታቸውን የሚመዘግብ ቴክኖሎጂ ፈጥራለች

Home of best apps

ቻይና ፊት በማየት ብቻ መላ ህዝቧን በአንድ ሰከንድ ውስጥ ማንነታቸውን የሚመዘግብ ቴክኖሎጂ ፈጥራለች

አዲስ አበባ መጋቢት 20፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና የክትትል ስርዓቷን ለማሻሻልና ለማሳደግ የሰው ማንነት በፊቱ መለየት የሚያስችል ቴክኖሎጂ መፍጠሯ ተነገረ።

ይህ ስርዓት 1 ነጥብ 4 ቢለየኑን የቻይና ህዝብ በአንድ ሰከንድ እና የአለምን ህዝብ በ2 ሰከንድ ማወቅ ያስችላል ተብሏል።

የሰውን ማንነት በፊት ማወቅ የሚያስችለው ይህ ስርዓት የክትትል ካሜራዎችን በቻይና ተደራሽ ለማድረግ በፈረጆንቾቹ 2005 የተከፈተው የስካይኔት ፕሮግራም አካል መሆኑ ተነግሯል።

ቻይና በአሁኑ ወቅት 170 ሚሊየን የክትትል ካሜራዎችን በስራ ላይ ማዋሏ የተነገረ ሲሆን፥ በ2020 ይህን የካሜራ ቁጥር እስክ 570 ሚሊየን የማድረስ እቅድ እንዳላት ነው የሚነገረው።

ይህም ቻይና በአንድ ካሜራ ሁለት ዜጎቾን መከታተል ያስችላታል ነው የተባለው።

ቻይና ሰውን በፊቱ ማወቅ የሚያስችለውን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ባለፉት ሁለት አመታት ከ2 ሺህ በላይ ወንጀለኞችን ማሰሯ ተገልጿል።

በዚህ ፈጣን የክትትል መሳሪያው በመጠቀም ቻይና ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን፣ የጠፉ ሰዎች ለማፈላለግ እና ሊከሰቱ የሚችሉ ወንጀሎችን ለመገመት እየተጠቀመችበት እንሚገኝም ተነግሯል።

የመሳሪያው ውጤታማነት 99 ነጥብ 8 በመቶ የተረጋገጠ ሲሆን፥ በየትኛው ስፋራ ያለገደብ ለመጠቀም የሚመች እንደሆነ ታውቋል።

ይህ መሳሪያ ቻይና በሰው ሰራሽ የድህነት አገልግሎት ቀዳሚ ለመሆን ከምታደርገው ተግባር አንዱ ክፍል መሆኑ ተጠቁሟል።

ለዚህም ባለፈው አመት ቻይና ከአሜሪካ አምስት እጥፍ ብልጫ በዚሁ ዘርፍ ለሚሰማሩት ፍቃድ መስጠቷ ተጠቅሷል።

ምንጭ፦fossbytes.com