ቦይንግ የመረጃ መረብ ጥቃት እንደተቃጣበት አስታወቀ

Home of best apps

ቦይንግ የመረጃ መረብ ጥቃት እንደተቃጣበት አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ግዙፉ የአውሮፕላን አምራች ኩባንያ ቦይንግ የመረጃ መረብ ጥቃት እንደተቃጣበት አስታወቀ።

ኩባንያው በተወሰነ የአሰራር ስርዓቱ ላይ እክል የፈጠረ የመረጃ መረብ ጥቃት እንደተፈጸመበት መለየቱን የኩባንያው ምክትል ፕሬዚዳንት ተናግረዋል።

ምክትል ፕሬዚዳንቷ ሊንዳ ሚልስ እንዳሉት፥ የተፈጸመው ጥቃት የተወሰነ የአሰራር ስርዓቱ ላይ እክል ከመፍጠር ያለፈ ጉዳት አላደረሰም።

በኩባንያው ላይ የተቃጣውን የመረጃ መረብ ጥቃት በተመለተ በአንዳንድ ሚዲያዎች የቀረበው መረጃ ግን በጣም የተጋነነ እና ትክክል ያልሆነ ነው ብለዋል።

የመረጃ መረብ ጥቃቱ በተወሰነ የኩባንያው ስርዓት ላይ መጠነኛ ጉዳት ማድረሱንም ነው የተናገሩት።

ከዚህ ጋር ተያይዞም አሁን ላይ የማስተካከያ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።

አሁን ቦይንግ ላይ የተፈጸመው የመረጃ መረብ ጥቃይ ዋና ክራይ በመባል የሚታወቀው ቫይረስ ሳይሆን እንደማይቀር የተለያዩ ሚዲያዎች እየዘገቡ ነው።

ይህ የቫይረስ ጥቃት ኮምፒውተሮችን በመመቆለፍና አገልግሎት እንዳይሰጡ በማድረግ የአንድ ኩባንያ ወይም ተቋምን አገልግሎት ማቋረጥን አላማው ያደረገ ነው።

ይህን የሚፈጽሙ መረጃ በርባሪዎችም ኮምፒውተሮችን በመቆለፍ ያቋረጡትንና ያስተጓጎሉትን ስራ ለማስጀመር በርካታ ገንዘብ ይጠይቃሉ።

የገንዘብ ተቋማትን ጨምሮ በርካታ ኩባንያዎችና ተቋማት እስካሁን በዚህ የመረጃ በርባሪዎች ጥቃት ሰለባ መሆናቸው ይነገራል።

ምንጭ፦ Reuters እና theverge.com/