አፕል እንደ መፅሃፍ የሚታጠፍ ስማርት ስልክ እየሰራ መሆኑ ተነገረ

Home of best apps

አፕል እንደ መፅሃፍ የሚታጠፍ ስማርት ስልክ እየሰራ መሆኑ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ግዙፉ የስማርት ስክል አምራች አፕል ፊቱን ወደ ታጣፊ ስማርት ስልኮች ማዞሩ እየተነገረ ነው።

ኩባንያው አዲስ እየሰራ ነው የተባለው አይ ፎን ስማርት ስልክ ልክ እንደ መፅሃፍ የሚታጠፍ እና የሚዘረጋ መሆኑንም መረጃዎች ጠቁመዋል።

በእሲያ ሀገራት የሚገኙ በርካታ ጥሬ እቃ አቅራቢ ኩባንያዎችም ከአፕል ጋር በመሆን በታጣፊ ስማርት ስልክ ዙሪያ እየሰሩ መሆኑን አረጋግጠዋል ነው የተባለው።

የአፕል ምርት የሆነው ታጣፊው አይ ፎን ስማርት ስልክም እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2020 ለገበያ ይቀርባል ተብሎም ተጠብቋል።

አፕል እየሰራው ነው የተባለው ታጣፊ ስማርት ስልክ በሚታጠፍበት ጊዜ የመደበኛ ስማርት ስልክ መጠን ሲኖረው፤ ሲዘረጋ ግን የታብሌት መጠን ይኖረዋል ተብሏል።

በአሁኑ ወቅ ኩባንያዎች በታጣፊ ስማርት ስልክ ዙሪያ እየሰሩ ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ ሳምሰንግ፣ ሌኖቮ፣ ዜድ ቲ እና ኤል ጂ ተጠቃሽ ናቸው።

ምንጭ፦ www.dailymail.co.uk