የሰዎችን የአካል እንቅስቃሴ ወደ ኤሌክትሪክ ሀይል ቀይሮ የሚጠቀመው የስፖርት ማዘውተሪያ

Home of best apps

የሰዎችን የአካል እንቅስቃሴ ወደ ኤሌክትሪክ ሀይል ቀይሮ የሚጠቀመው የስፖርት ማዘውተሪያ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በለንደን ከተማ ቴራ ሀሌ የተባለ የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከል የደንበኞቹን የአካል እንቅስቃሴ ወደ ኤሌክትሪክ ሀይል በመቀየርና በመጠቀም የአካባቢ ብክለትን በመቀነስ ቦጎ አስተዋፅኦ አያበረከተ መሆኑ ተሰምቷል። 

 

ማዕከሉ የደንበኞች የአካል እንቅስቃሴ ወደ ኤሌክትሪክ ሀይል በመቀየር ሀይል መቆጥብና ማከማቸትም ችሏል ነው የተባለው።

የሰበሰበውን ሀይልም ለስፖርት ማዕከሉ ጥቅም ከማዋል ባለፈ በአካባቢው ለሚገኙ የቢዝነስ ተቋማት አገልግሎት እንደሚያውልም ታውቋል።

ማዕከሉ በለንደን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሀይልን በመጠቀም የመጀመሪያው ሲሆን፥ ኩባንያው ከፈረንጆቹ ሚያዚያ 12 በኋላ በሌሎች ከተሞች እንደሚከፍት አስታውቋል ተብሏል።

የአካባቢ ብክለትን በመከላከል ከደንበኞቹና ከአካል ብቃት አሰሪዎቹ በስድስት የስፖርት ማዕከል በ50 ደቂቃ ብቻ 1 ሺህ 500 እስከ 3 ሺህ 300 ዋት ኤሌክትሪክ ሀይል ማምረት እንደሚቻል ተመላከቷል።

በዚህም ለዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር 400፣ ለላፕቶብ 200፣ ለአምፖል 60 እና 1200 ዋቶችን ለጸጉር ማድረቂያ መጠቀም እንዳሚቻል በዘገባው ተጠቅሷል።

ማዕከሉ ከአካባቢ ብክለት የጸዳ ሀይል ከመጠቀሙም ባሻገር በአካባቢው የወዳደቁና አገልግት ላይ የማይውሉ ቁሳቁሶችን ውስጡን ለማስጌጥ እንደተጠቀመ ነው ዘገባው የሚያስረዳው።

የማዕከሉ ዙሪያ ጠርዞች ከአገለገሉ የጣውላ መገልገያዎች፣ ወለሉ ደግሞ ከአገለገሉ ፕላስቲኮች የተሰሩ ናቸውም ተብሏል።

ግድግዳው በሙሉ ንጹህ ኦክስጅንን ለማግኘት በሚረዱ አረንጓዴ እፀዋት የለበሰ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ማዕከሉ ተፈጥሮዊና ምቾት ከሚሰጡ አረንጓዴ ነገሮች የተገነባ ነው።

ምንም እንኳ ማዕከሉ አረንጓዴ ከሆኑ ነገሮች የተገነባ ቢሆንም በሌሎች ማዕከሎች የሚሰጡ የተሟሉና ዘመናዊ አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ ዘገባው አስረድቷል።

 

ምንጭ፦ huffingtonpost.co.uk

 

ተተርጉሞ የተጫነው፦ በእንቻለው ታደሰ