የተሽከርካሪዎች ዘመናዊ የፊት መብራቶች በአሽከርካሪዎች እይታ ላይ ተጽህኖ እየፈጠሩ ነው ተባለ

Home of best apps

የተሽከርካሪዎች ዘመናዊ የፊት መብራቶች በአሽከርካሪዎች እይታ ላይ ተጽህኖ እየፈጠሩ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የምራባዊያኑ የተሽከርካሪ ኢንሹራስ ኩባንያዎች ጥናት እንዳመላከተው 15 በመቶ አሽከርካሪዎች በዘመናዊ የፊት መብራቶች አማካኝነት እይታቸው ላይ ችግር እያደረሰ ነው ብለዋል።

ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ላይ የሚገጠሙ የፊት መብራቶች ብርሀን በሌሎች አሽከርካሪዎች እይታ ላይ ለተወሰነ ጊዜ ችግር የሚፈጥርና እይተቻው ወደ ቀድሞው ሁኔታ እስኪመለስ ድረስ በርካታ ሴኮንዶች እንደሚወስድ የኢንሹራስ ኩባንያዎች ያጠኑት ጥናት አመላክቷል።

በ2 ሺህ 61 አሽከርካሪዎች ላይ በተደረገ የጥናት ውጤት እንደተገለጸው ዘመናዊ የፊት መብራቶች የመንገድ ደህንነት አደጋ ሆነው ተስተውለዋል።

የተሽከርካሪ ኩባንያዎች ቀድሞ ይጠቀሙባቸው በነበሩ የፊት መብራቶች ፋንታ ዘማናዊ የፊት መብራቶችን እየተጠቀሙ ሲሆን፥ መብራቱ የተገጥመለትን ተሽከርካሪ ለሚጠቀሙ አሽከርካሪዎች ምቹ ቢሁኑም በአንጻሩ ከተቃራሪ አቅጣጫ ለሚመጡት ግን ምቾት የሌላቸውና ለአደጋ የሚያጋልጡ ናቸው ነው የተባለው።

በጥናቱ 65 በመቶ ያህል አሽከርካሪዎች ከተቃራኒ አቅጣጫ የሚመጡ ዘመናዊ የፊት መብራቶች ብርሀን ከፍተኛ መሆኑን ሲናገሩ፤ 58 በመቶ ያህሉ ደግሞ የብርሀኑ መጠን መብዛት ብቻ ሳይሆን ለአደጋ እንደሚያገልጡም ተናግራዋል።

በዘመናዊ የፊት መብራቶች እይታችን ይሰተጓጎላል ያሉት ጥናቱ የተካሄደባቸው አሽከርካሪዎች፥ አይታቸው ወደ ቀድሞው ሁኔታ እስኪመለሰ 5 ሰከንድ ያህል ጊዜ እንደሚወስድባቸው ተናግረዋል።

ጥናቱ ከተካሄደባቸው 10 አሽከርካሪዎች አንዱ ለዘመናዊ የፊት መብራቶች ብርሃን ከተጋለጡ በኋላ እይታቸው ወቀድሞ ሁኑታ እስኪመለስ እስከ 10 ሰከንድ ይወስድብናል ያሉ ሲሆን፥ 16 በመቶ ያህል ደግሞ አንድ ሰከንድ እንኳ የማይፈጅባቸው መሆኑን ተናግረዋል።

በጥናቱ በእድሜ የገፉ አሽከርካሪዎች የበለጠ የችግሩ ተጠቂዎች እንደሆኑ ዘገባው አስረደቷል።

ጥናት ከተደረገባቸው 15 በመቶ ያህል አሽከርካሪዎች ደግሞ የዘመናዊ የፊት መብራቶች ለአደጋ የሚያጋልጡት የብርህን መብዛት ነው ሲሉ አስረድተዋል።

የኢንሹራንስ ኩባንያው የመንገድ ደህንነት ቃል አቀባይ ፔተ ውሊያም እንደተናገሩት አንዳንድ ተሽከርካሪዎች የሚጠቀሟቸው ዘመናዊ የፊት መብራቶች ለመንገድ ተጠቃሚውች አስቸጋሪ ናቸው።

የፊት መብራቶቹ ሲሻሻሉ የመንገድ ደህንነትን ያገናዘቡ መንገዶችን በጋራ ለመጠቀም የሚያስችሉና የአሽከርካሪዎቹን ደህንነት አደጋ ላይ የማይጥሉ መሆን አለባቸው በለዋል።
አሽከርካሪዎችም ሌሎች አሽከርካሪዎች ላይ ብርሀን በመልቀቅ ችግር እንዳይፈጥሩ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የፊት መብራት አጠቃቀም የራሱ ህግ ያለው ቢሆንም፤ በተለያየ የእድሜ ደረጃ ላይ የሚገኙ አሽከርካሪዎች የተለያየ አጠቃቀም ልምድ እንዳላቸው ዘገባው ያስረዳል።

 

ምንጭ፣ ሁፊንግቶን ፖስት

 

ተተርጉሞ የተጫነው፥ በእንቻለው