ኒሳን ከ2022 ጀምሮ በየአመቱ 1 ሚሊየን በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ለገበያ ሊያቀርብ ነው

Home of best apps

ኒሳን ከ2022 ጀምሮ በየአመቱ 1 ሚሊየን በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ለገበያ ሊያቀርብ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) መኪና አምራች ኩባንያ ኒሳን ከስድስት ወር በኋላ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን እንደሚያስተዋውቅና በቀጣይ አምስት አመታት የገበያ ሽፋኑን በስድስት እጥፍ ለማሰደግ አቅዶ እየሰራ ነው ተብሏል።

የጃፓኑ የተሸከርካሪ አምራች ኩባንያ በፈረንጆቹ 2023 ማብቂያ ላይ 1 ሚሊየን በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ለገበያ ከማቅረብ በተጨማሪ የኤሌክትሪክ ባቡሮችንም እንደሚያመርት ገልጿል።

ኩባንያው የተለያየ ብቃት ደረጃ ያላቸው ስምንት አይነት በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን እንደሚያመርት ማቀዱን አስረድቷል።

ቮልስዋገን፣ ጄኔራል ሞተርስና የቻይና ኩባንያዎች የዘርፉን ገበያ እያጣበቡት የመጡ ሲሆን፥ ኒሳን ኩባንያ ይዞት የሚመጣው የቴክኖሎጂ አማራጭ ገበያውን ለመምራት እንደሚያስችለው ተጠቁሟል።

ኒሳን በአሜሪካና በአካባቢው ገበያ ያለው ተፈላጊነት እየቀነስ መምጣቱ የተገለጸ ሲሆን፥ ባለፉት አምስት አመታት የቻይና ደንበኞቹ እንዳይርቁት ለማድረግም 9 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ወጪ አድርጓል።

የኩባንያው ዋና የእቅድ ባለሞያ ፒሊፔ ከሌን ባለፈው አርብ ቶኪዮ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ኩባንያው በዘርፉ ከቻይና ኩባንያዎች ጋር የሚካሄደውን የገበያ ውድድር በዚህ አመት በኒሳን ኩባንያ የሚመራ ይሆናል ብለዋል።

በኤልክትሪክ የሚሰሩት የኩባንያው ውጤቶች የቻይና ደንበኞችን የገበያ ፍላጎትና ሞዴለ ምርጫ ባገናዘበ መንገድ የሚፈበረኩ መሆኑንና ሞዴሎቹ በቨኑሲያ የንግድ ምልክት እንደሚሰሩም አስታውቀዋል።

የተሽከርካሪ አምራች ኩባንያዎች ባለፈው አመት ብቻ ለቻይና 1 ነጥብ 52 ሚልየን፣ ለአሜሪካ 1 ነጥብ 59 ሚሊየን ተሽከርካሪዎችን ለገበያ አቅርበዋል።

ቻይና በ2022 ከዘርፉ 16 ነጥብ 5 ትሪሊየን ዬን በማግኘት በአጠቃላይ በእቅድ ከያዘችው ገቢ አንድ ሶስተኛ ያህሉን ለመግኘት አቅዳለች ነው የተባለው።

በቻይና ገብያ ትልቁ የሆንው የጃባኑ ተሽከርካሪ አምራች ኒሳን በ2022፣ 20 በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ሞዴሎችን በማስተዋዎቅ ከፍተኛ ገቢ የማግኘት እቅድ አለው።

በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሸከረካሪዎችም በ2022 30 በመቶ የገብያ ድርሻ የሚይዙ ሲሆን፥ በ2025 የዘርፉ ገበያ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ይሸፈናል ሲል ኩባንያው አስታውቋል።

 

 

 

ምንጭ፣
የተተረጎመው፣ በእንቻለው ታደሰ