የቻይናው ባይዱ ኩባንያ አሽከርካሪ አልባ ተሽከርካሪዎችን ለመጀመርያ ጊዜ በጎዳና ላይ መሞከር ጀመረ

Home of best apps

የቻይናው ባይዱ ኩባንያ አሽከርካሪ አልባ ተሽከርካሪዎችን ለመጀመርያ ጊዜ በጎዳና ላይ መሞከር ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይናው ግዙፉ ኢንተርኔት ቴክኖሎጂ ኩባንያ ባይዱ፥ ለመጀመርያ ጊዜ አሽከርካሪ አልባዋን ተሽከርካሪ በቤጂን ጎዳናዎች መሞከር ጀምሯል።

ሙከራው ባለፈው ሳምነት የዮበር ኩባንያ ውጤት የሆነችው አሽከርካሪ አልባ ተሽከርካሪ ጎዳና ላይ የትራፊክ አደጋ በማድረስ የአንድ ሰው ህይወት ካጠፋች ከቀናት በኋላ የተደረገ ነው ተብሏል።

በቤጂንግ የአሽከርካሪዎች ህግ መሰረት አሽከርካሪ አልባዋ ተሽከርካሪ ፈቃድ ከመስጠቷ በፊት 5 ሺህ ኪሎ ሜትር መጓዝ አለባት።

በዚህም ተሽከርካሪዋ ሰዎች በማይደርሱበት ቦታ በሙከራ ላይ መሆኗ ነው የተገለፀው።

በተጨማሪም የትራፊክ ህግን፣ ያለ አሽከርካሪ የመሽከርከር ብቃትና በአደጋ ጊዜ በሰው ጉልበት ሀይል ማቋረጥ የሚያስችላትን ብቃት ተፈትሻ ማለፍ እንዳለባት ተገልጿል።
በማንኛውም ሰአት እራሷን በራሷ ለመቆጣጠር የሚያስችላትን ከ50 ሰአት ያላነሰ ሙከራም ታድርገላች ተብሏል።

በዚህም ሁሉም አሽከርካሪ አልባ ተሽከርካሪዎች ጎዳናዎች ላይ ከመውጣታቸው በፊት በዘርፉ ባለሞያዎች ምርመራ ሊደረግባችው እንደሚገባ ተጠቁሟል።

ምርመራውም በቴክኖሎጂ የተደገፈና አሽከርካሪ አልባ ተሽከርካሪዋ በአግልግሎት ላይ የሚጠበቁ ተግባራትን በትክከል ማከናወን የምትችል ስለመሆኑ በትኩረት መታየት አለባት።

የቤጂንግ ከተማ አስተዳደር መረጃ እንደሚያመላክተው በቤጅንግ ከተማ አሽከርካሪ አልባ ተሽከርካሪዎች ሙከራ የሚያደርጉበት መንገድ ግንባታ ተጠናቋል።

በድምሩ 105 ኪሎ ሜትር የሆኑ 33 መንገዶች ለሙከራ ዝግጁ ሆነዋል፤ ለነዋሪዎቹ ደህነነት ሲባልም ሙከራው ተግባራዊ የሚደረገው ከቤጂንግ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኙ መንገዶች ላይ ነው ተብሏል።

ምንጭ፣ ሲጂቲኤን
የተተረጎመው፣ በእንቻለው ታደሰ