ሩሲያ ሰው የያዘ መንኩራኩር ወደ ዓለም አቀፉ የህዋ ምርምር ማዕከል አመጠቀች

Home of best apps

ሩሲያ ሰው የያዘ መንኩራኩር ወደ ዓለም አቀፉ የህዋ ምርምር ማዕከል አመጠቀች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2010 (ኤፍቢሲ) ሩሲያ ሰው የያዘ መንኩራኩር ካዛኪስታን ከሚገኝ ማዕከል ወደ ዓለም አቀፉ የህዋ ተቋም ማምጠቋን አስታወቀች።

መንኩራኩሯ ወደ ህዋ ስትመጥቅ ሦስት ባለሙያዎችን ጭናለች ተብሏል።

አንደኛው ከሩሲያው የህዋ ማዕከል ከሮስኮስሞስ ሲሆን ሁለቱ ደግሞ ከአሜሪካው ናሳ መሆናቸው ተገልጿል።

በቆይታቸው ወደ 250 የሚደርሱ ሳይንሳዊ ምርምሮችን እንደሚያካሂዱ ተነግሯል።

ከእነዚህም መካከል ስነ-ህይወት፣ የስነ-ምድር ሳይንስ፣ በሰው ልጅ ላይ ያተኮረ ምርምርና በቴክኖሎጂ ዕድገት ላይ ያተኩራል ተብሏል።

ሶዩዝ ኤምኤስ-08 መንኮራኩር ይመጥቃል ተብሎ የታሰበው ባለፈው ዓመት ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ወደዚህ ቀን መዛወሩን ይናገራሉ።

አዲሶቹን ተጓዦች ጨምሮ በዓለም አቀፉ የህዋ ተቋም ያሉ ተመራማሪዎች ቁጥር ስድስት መድረሱ ተገልጿል።

ተጓዦቹ ከአምስት ወራት ቆይታ በላይ ይኖራቸዋል ተብሏል።

ዓለም አቀፉ የህዋ ምርመር ተቋም በ15 አገራት የተቋቋመ ሲሆን፥ በዋናነት በናሳ በሮስኮስሞስና በአውሮፓ የህዋ ማዕከል ይመራል። የሰው ልጅ ወደ ህዋ ካመጠቃቸው ምርመሮች ሁሉ ግዙፉ እንደሆነም ይነገርለታል።

እስካሁን 280 ሰዎች ተቋሙን ጎብኝተውታል።

 

 

 

 

 

ምንጭ፦ ከዓለም አቀፉ የህዋ ተቋም፣ከናሳና ከሲጂቲኤን
ተተርጉሞ የተጫነው፦ በአብረሃም ፈቀደ