የአለማችን ትንሿ ኮምፒውተር ይፋ ተደረገች

Home of best apps

የአለማችን ትንሿ ኮምፒውተር ይፋ ተደረገች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሜሪካው አይ ቢ ኤም ቴክኖሎጂ ኩባንያ የተመረተችው የአለማችን ትንሿ ኮምፒውተር ይፋ ተደረገች።

እጅግ በጣም ትንሽ እና በየትም ቦታ ለማስቀመጥ ትመቻለች የተባለችው ኮምፒውተር አይ ቢ ኤም ባዘጋጀው ብሄራዊ ጉባኤ ላይ ይፋ ተደርጋለች።

 ኮምፒውተሯ በመጠኗ ትንሸ ብትሆንም አስገራሚና ከዚህ በፊት ከነበሩ ኮምፒውተሮች ጋር የመወዳደር አቅም እንዳላት ተነግሯል።

ይህቺ ትንሽ ኮምፒውተር በእይታ ለመለየት አስቸጋሪ በመሆኗ ለመጠቀም የአጉሊ መነፀር ድጋፍ ሊያስፈልግም ይችላል ተብሏል።

በመቶ ሺህ የሚቆጠር ማስተላለፊያዎች ትይዛለች ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፥ መረጃዎችን ለመከታተል፣ ለመተንተን እና ሌሎች ተግባራት ለመከወን ታስችላለች።

እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ የሚከናወኑ ግብይቶችን ሚስጥራዊነትን በመጠበቀ መንገድ ለመስራት ሚናዋ የጎላ መሆኑ ተነግሯል።

በመጪዎቹ አምስት አመታት ከዚህም ያነሰ መጠን ያላት ኮምፒውተር ኩባንያው ሊያመርት እንደሚችል አስታውቋል።

ምንጭ፦ ቴክዋርም