ፌስቡክ በአሜሪካ የፌዴራል የንግድ ኮሚሽን እየተመረመረ ነው

Home of best apps

ፌስቡክ በአሜሪካ የፌዴራል የንግድ ኮሚሽን እየተመረመረ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ50 ሚሊየን ሰዎች የፌስቡክ አድራሻ በአንድ የፖለቲካ አማካሪ ተቋም እንደተበረበረ መገለፁን ተከትሎ የአሜሪካ የንግድ ኮሚሽን በፌስቡክ ላይ ምርመራ እያካሄደ ነው።

ምርመራውን የሚያደርገው የአሜሪካ ንግድ ኮሚሽን ለደንቦኞች ጥበቃ የሚያደርግ ገለልተኛ መንግስታዊ ተቋም ነው።

ካንብሪጅ አናሊቲካ የተሰኘው ኩባንያ በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የ50 ሚሊየን ሰዎችን ግለሰባዊ መረጃዎች በመበርበር ለቅስቀሳ ተጠቅሟል የሚል ክስ ቀርቦበታል።

ይህንን ተከትሎም የኩባንያው መሪ ከቦርድ አባልነት መታገዱ ተጠቁሟል።

ይህ የመረጃ ብርበራ የግለሰቦችን መረጃ በፍቃዳቸው ማሰስ እንዲቻል ተደርጎ እንደ አውሮፓውያኑ ዘመን ቀመር በ2013 በተዘጋጀ መተግበሪያ መከናወኑ ታውቋል።

ኩባንያውም ለፕሬዚዳንት ዶናልድ ትርምፕ የምርጫ ዘመቻ ምንም አይነት የግለሰብ መረጃ አለማቅረቡን ይገልፃል።

የግለሰቦቹ መረጃ መበርበሩ ይፋ ከተደረገ በኋላም የፌስቡክ የአክሲዮን ዋጋ መቀነሱ ነው የተነገረው።

የፌስቡክ ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ ለብሪታንያ እና አውሮፓ ፓርላማ በግለሰቦቹ መረጃ ብርበራ ዙሪያ ገላፃ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

 

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ