ቻይና ለጠፈር ምርምር የሚውሉ እጅግ ፈጣን አውሮፕላኖች የሚሞከሩበት ዋሻ ገነባች

Home of best apps

ቻይና ለጠፈር ምርምር የሚውሉ እጅግ ፈጣን አውሮፕላኖች የሚሞከሩበት ዋሻ ገነባች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቻይና ለጠፈር ምርምር የሚውሉ እጅግ ፈጣን የሚባሉ አውሮፕላኖች የሚሞከሩበት ዋሻን መገንባቷ ተገለፀ።

ዋሻው 265 ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን በሰዓት እስከ 30 ሺህ 625 ኪሎ ሜትር የሚምዘገዘጉ አውሮፕላኖችን የመሞከር አቅም አለው ነው የተባለው።

በዋሻው ተፈጥሯዊ የአየር ግፊት እንዲኖር በማድረግ አውሮፕላኑ ሊያጋጥመው በሚችለው የዓየር ሁኔታ ውስጥ እንዲሞከር የሚያስችልም ነው።

ባለፈው ወር እጅግ ፈጣን የሆነ አውሮፕላንን በዋሻው እንደተሞከረ ተገልጿል።

ይህ እጅግ ፈጣን አውሮፕላን ከቤጂንግ ኒውዮርክ በ2 ሰዓት ውስጥ መግባት የሚችል ነው። በሰዓትም 9 ሺህ 12 ኪሎ ሜትር የሚጓዝ ነው።

አዲሱ ቴክኖሎጂ ቻይና ሌሎች አገራትን በዘርፉ እንድትመራ የሚያስችላት መሆኑ ተገልጿል።

 

 

 

 

ምንጭ፦ ሲጂቲኤን
ተተርጉሞ የተጫነው፦ በአብረሃም ፈቀደ