ኤች.ፒ ለመረጃ ጠላፊዎች 10 ሺህ ዶላር ሊሸልም መሆኑ ተነግሯል

Home of best apps

ኤች.ፒ ለመረጃ ጠላፊዎች 10 ሺህ ዶላር ሊሸልም መሆኑ ተነግሯል

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 30፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኤች.ፒ የተባለው የቴክኖሎጂ ቁሶች አምራች ኩባንያ በማተሚያ ማሽን (ፕሪንተር) ምርቱን በመጥለፍ ክፍተቱን ለሚያመላክቱ የመረጃ ጠላፊዎች 10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ሊሸልም መሆኑ ተነግሯል።

በዚህም ኤች ፒ ኩባንያ የፕሪንተር ምርቶችን ለሚጠልፉ የመረጃ በርባሪዎች ዳጎስ ያለ የገንዘብ ሽልማት ያቀረበ የመጀመሪያው ኩባንያ መሆን ችሏል ነው የተባለው።

እንደ ኤች ፒ ገለፃ፥ ኩባንያው በፕሪንተር ምርቱ ላይ የሚስተዋል የመጠለፍ ክፍተቶችን ለመለየት 10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ለመረጃ በርባሪዎች በሽልማት መልክ ሲያዘጋጅ ይህ የመጀመሪያው ነው።

የኤች ፒ ኩባንያ ዋና ቴክኖሎጂስት ሻይቫውን አልብራይት እንደተናገሩት፥ በአሁኑ ወቅት በሳይበሩ ዓለም የሚፈፀሙ ወንጀሎች እየተበራከተና እየረቀቀ በመምጣቱ ሽልማት የሚያስገኝ ስራ ማዘጋጀት የኩባንያውን ተአማኒነት ይጨምራል።

ኤች ፒ በዓለማችን ላይ ደህንነቱ የተጠበቀ ማተሚያ (ፕሪንተር) ለማቅረብ የሚያደርገውን ስራ የሚያግዝ መሆኑንም ተናግረዋል።

ኩባንያው አሁን ባዘጋጀው ውድድር መሰረትም የመረጃ መዝባሪዎች አሊያም የቴክኖሎጂው ዘርፍ ተመራማሪዎች በፕሪንተሩ ላይ በሚያደርጉት ሙከራ የሚያገኙበትን የጥቃትት ተጋላጭነት ለኩባንያው የሚያቀርቡ ይሆናል።

በዚህም መሰረት ኩባንያው ቀድሞ ከለያቸው ተጋላጭነት ጋር ካመሳከረ በኋላ ተወዳዳሪዎች ያቀረቡለት ተጋላጭነት አዲስ ሆኖ ከተገኘ የገንዘብ ሽልማቱን የሚያበረክት ይሆናል።

የገንዘብ ሽልማቱን እንደ ተጋላጭነቱ ክብደት ከ5 ሺህ እስከ 10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር እንደሚደርስም ኩባንያው አስታውቋል።

ምንጭ፦ www.techworm.net

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *