የቻይናው ዲዲ ኩባንያ የተሽከርካሪ አገልግሎቱን ለማዘመን የ1ቢሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት ይፋ አደረገ

Home of best apps

የቻይናው ዲዲ ኩባንያ የተሽከርካሪ አገልግሎቱን ለማዘመን የ1ቢሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 30፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቻይናው ዲዲ ኩባንያ የተሽከርካሪ አገልግሎቱን ለማዘመን የ1ቢሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት ይፋ አድርጓል።

በቻይና የተሽከርካሪ አገለግሎት ላይ የተሰማራው ዲዲ ኩባንያ አገልግሎቱን ለማዘመንና የንግድ ምልክቱን ለማደስ የአንድ ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ኢንቨስትመን ይፋ አድርጓል።

 ኩባንያው የተሽከርካሪ ሊዝ ሽያጭ፣ ጥገና እና የጋዝ ማደያ አገልግሎት ላይ የተሰማራ ሲሆን፥ ዓመታዊ የአገልግሎት ገቢው 8 ነጥብ 79 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር መሆኑን አስታውቋል።

አሁን ላይ ለ30 ሚሊየን ያህል አሽከርካሪዎች ዘመናዊና ታዓማኒ አገልግሎትን ለመስጠት በሚያስችለው ቅድመ ዝግጅት ላይ መሆኑም ነው የተገለጸው።

ኩባንያው በሚቀጥለው ዓመት ቁጥር አንድ አገልግሎት ሰጪ ሆኖ ለመገኘት ዝግጅት ላይ ሲሆን፥ የንግድ ምልክቱም ከዲዲ ወደ ዢያውጁ እንሚቀይር ዘገባው ያስረዳል።

ምንጭ፦ reuters.com

የተተረጎመውና የተጫነው፦ በእንቻለው ታደሰ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *