ናሳ ከምንጊዜውም ይልቅ ወደ ፀሐይ መቅረብ የሚያስችለውን መንኩራኩር ሊያመጥቅ ነው

Home of best apps

ናሳ ከምንጊዜውም ይልቅ ወደ ፀሐይ መቅረብ የሚያስችለውን መንኩራኩር ሊያመጥቅ ነው

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 27፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ናሳ በሚቀጥለው ሳምንት ከምንጊዜውም ይልቅ ወደ ፀሐይ መቅረብ የሚያስችለውን መንኩራኩር ሊያመጥቅ መሆኑን አስታወቀ፡፡

በቆይታውም የፀሐይን ከባቢ አየር ወይንም ውጫዊ አካል ያጠናል ተብሏል፡፡

ፓርከር ሶላር የተሰኘው መንኩራኩር ከስምንት ቀናት በኃላ ከፍሎሪዳ ግዛት እንደሚነሳ ተገልጿል፡፡

በመሬትና በፀሐይ መካከል ያለው አማካይ ርቀት 150 ሚሊየን ኪሎሜትር እንደሚደርስ ይታመናል፡፡

አዲስ የሚላከው መንኩራኩር ታዲያ ከፀሐይ 6 ነጥብ 1 ሚሊየን ኪሎሜትር ርቀት ላይ በመሆን ነው መረጃዎችን ይሰበስባል ተብሎ የሚጠበቀው፡፡

ይህ አዲሱ የናሳ ፕሮጀክት በጥቅሉ ወድ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር እንደሚፈጅ ተነግሮዋል፡፡

 

 

ምንጭ፦አልጀዚራ
አብርሃም ፈቀደ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *