ታላላቅ ኩባንያዎች የደንበኞች የመረጃ ነፃነት ጥበቃ ህግ ለማውጣት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከትራምፕ አስተዳደር ጋር እየመከሩ ነው

Home of best apps

ታላላቅ ኩባንያዎች የደንበኞች የመረጃ ነፃነት ጥበቃ ህግ ለማውጣት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከትራምፕ አስተዳደር ጋር እየመከሩ ነው

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 23፣ 2010 (ኤፍ.ቢሲ) ታላላቅ ኩባንያዎች የደንበኞች የመረጃ ነፃነት ጥበቃ ህግ ለማውጣት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከትራምፕ አስተዳደር ጋር እየመከሩ ነው ተብሏል።

ምክረ ሀሳቡ የበይነ መረብ ተጠሚዎችን የመረጃ ነፃነት መብት ለማስከበር የሚያስችል ህግ ለማርቀቅ መሆኑ ነው የተገለጸው።

በዚህም ባለፈው ወር ብቻ ከ80 ኩባንያዎች ከተውጣጡ ተወካዮች ጋር 22 ያህል ስብሰባዎች መካሄዳቸውን የሀገሪቱ የቴሌኮሚዩኒኬሽንና የመረጃ አስተዳደር መረጃ የሚያመላክተው። 

አሁን ላይ በአላም አቀፍ ደረጃ የግለሰባዊ የመረጃ ብርበራ ጥቃት እየተሰፋፋ ሲሆን፥ ባለፉት ጊዚያት በፌስቡክ ኩባንያና በሌሎች ተመሳሰይ ኩባንያውች ላይ የተከሰቱ ችግሮ ለዓብነት ተጠቅሰዋ።

በዚህም የአሜሪካ የንግድ ክፍል ከፌስ ቡክ፣ ጎግል ኩባንያዎችና ከሌሎች የበይነ መረብ አገልገሎት ሰጪዎች ጋር ባለፉት ሶሰት ወራት ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተመለከተ ግንኙነት ማድረጉ ነው የተገለፀው።

የግንኙነቱና የውይይቱ ዓላማ የዘርፉን የመረጃ ነፃነት ህግ ለማርቀቅ መሆኑን ነው ዘገባው የሚያላክተው። 

የደንበኞች የመረጃ አያያዝ በተመለከተ የዘርፉ አገልግሎት ሰጪ ኩባንያዎችን ለመከታተል የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ የሌለ መሆኑም ታውቋል።

የአውሮፓ ህብረት የደንበኞች አገልግሎት የመረጃ ጥበቃ ህግ አውጥቶ ተግባራዊ ስለማድረጉ በዘገባው አስታውሷል።

 

ምንጭ፦  foxnews

የተተረጎመውና የተጫነው፦ በእንቻለው ታደሰ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *