ፌስቡክ በቻይና ቢሮውን ለመክፈት አቅዷል

Home of best apps

ፌስቡክ በቻይና ቢሮውን ለመክፈት አቅዷል

አዲስ አበባ፣ ሀምሌ፣18፣2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፌስቡክ አገልግሎቱን በማይሰጥባት ቻይና ትርፋማ በሆነው ገበያ ለመሳተፍ ፈቃድ በማግኘቱ ቢሮውን በቅርቡ እንደሚከፍተ ተገለፀ።

ኩባንያው በቻይና የሚከፍተው ቢሮ ቻይናውያን አበልፃጊዎችና ስራ ፈጣሪዎችን ለመደገፍ የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል።

በቻይና የሚከፈተው ይህ ቢሮ ለኩባንያው የመጀመሪያው እንደሚሆንም ነው የተነገረው።

ቻይና በአለም አቀድ ደረጃ ከፍተኛ የሆነ የማህበራዊ መገናኛ ብዙሀን ንግድ ያለባት ቢሆንም ትዊተር፣ ፌስቡክ እና ዩቲዩብ የታገዱ ናቸው ተብሏል።

በዚህም ቻይናውያን የማህበራዊ መገናኛ ብዙሀን ተጠቃሚዎች ዌኢቦ፣ ሬነሬን እና ዩኩት የተባሉ በመንግስት ክትትል የሚደረግባቸውን ሚዲያዎች እንደሚጠቀሙ ይጠቀማሉ።

የፌስቡክ ኩባንያ መስራችና ስራ አስፈፃሚ ማርክ ዙከርበርግ የቻይና ባለስልጣናት በማግባባት ቢሮውን ለመክፈት የማንደሪን ቋንቋን አስከ መማር ደርሷል ተብሏል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *