በሲንጋፖር የ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ግለሰቦች የጤና ነክ መረጃ ተበርብሯል

Home of best apps

በሲንጋፖር የ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ግለሰቦች የጤና ነክ መረጃ ተበርብሯል

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 17 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) መረጃ በርባሪዎች በሲንጋፖር የማህበረሰብ ጤና አገልግሎት ማዕከል ላይ የመረጃ ምዝበራ ማድረሳቸው ተነገረ።

መረጃ በርባሪወቹ ባደረሱት ጥቃት ሳቢያም የ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ግለሰቦች የጤና መረጃን በርብረዋል።

የሲንጋፖር ጤና ጥበቃ መስሪያ ቤት ባለስልጣናት እንዳስታወቁት፥ የሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ሲዬን ሉንግ የጤና መረጃዎችም የመረጃ በርባሪዎቹ ሰለባ ሆነዋል።

የጤና መረጃቸው በመረጃ በርባሪዎቹ የተመዘበረባቸው ግለሰቦች ከፈረንጆቹ 2015 ግንቦት እስከ ሃምሌ ወር፥ እንዲሁም ካለፈው ግንቦት ወር መጀመሪያ ጀምሮ በተለያዩ ሆስፒታሎች የታከሙና የተገለገሉ ናቸው ተብሏል።

የግለሰቦች ስም፣ አድራሻ እና አጠቃላይ መረጃዎችም የመረጃ በርባሪዎቹ ኢላማ ሆነዋልም ነው የተባለው።

ከዚህ ባለፈም ግለሰቦቹ በህክምና ወቅት የታዘዘላቸው መድሃኒት አይነትና ያደረጉትን ህክምና የተመለከቱ መረጃዎችም ተበርብረዋል።

ይሁን እንጅ ከመረጃ ምዝበራው ጋር በተገናኘ በህክምና ላይ ስህተት ሊያስከትል የሚችል አጋጣሚ አመለከሰቱንም የሃገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ከሃገሪቱ ፖሊስ ጋር በተደረገ ማጣራት ምንም አይነት የህክምና ስህተት ሊያስከትል የሚችል አጋጣሚ አለመፈጠሩንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ሲንጋፖር የበርካታ ሃገር ጎብኝዎች መዳረሻ መሆኗን ተከትሎ ተመሳሳይ የመረጃ መረብ ጥቃቶች ሊኖሩ ይችላሉ በሚል ቅድመ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባም ባለስልጣናቱ አሳስበዋል።

አሁን ላይም ከተፈጠረው የመረጃ መረብ ምዝበራ ጋር በተያያዘ ያሉ ጉዳዮችን የማጣራት ስራ ተጀምሯል።

 

ምንጭ፦ latesthackingnews.com/

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *