ለ120 ቀናት በአየር ላይ መቆየት የሚችል አውሮላን የሙከራ በረራውን አደረገ

Home of best apps

ለ120 ቀናት በአየር ላይ መቆየት የሚችል አውሮላን የሙከራ በረራውን አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 16፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለ120 ቀናት በአየር ላይ መቆየት የሚችለው አውሮላን የሙከራ በረራውን ማድረጉ ተግልጿል።

ዘፔይር የተባለው አውሮፕላን በጸሃይ ሀይል የሚንቀሳቀስ ሲሆን፥ ለ120 ቀናት ያህል በአየር ላይ ለመቆየት እንደሚችል ነው የተገለጸው።

አዲሱ አውሮፕላን ቀንቀን የጸሃይ ሀልይልን በመጠቀም የሚንቀሳቀስ ሲሆን፥ ማታ ማታ የሚጠቀምበትን ሀይል ቀን ቀን በመሰብሰብ የጸሀይ ሀይልን ብቻ የሚጠቀም መሆኑን ነው ዘገባው የሚያመላክተው።

አውሮፕላኑ የኤር ባስ ኩበንያ ስሪት ሲሆን፥ ከተለመደው የአየር ትራፊክ መስመር ከፍታ በላይ በተለያዩ የአየር ጸባዩች ሁኔታ ውስጥም እንደሚበር ታውቋል።

ከረጅም ርቀት መረጃዎችን ለመለዋዎጥ የሚያስችሉ ሴንሰሮች የተገጠሙለት ሲሆን፥ ከባድ ጭነቶችን ለማስተናገድ እንደማይችል ተገልጿል።

የአው ሮፕላኑ 2ክንፎች ከ75 ኪሎ ግራም የማይበልጡ ሲሆን፥ ወደ ፊትም ሌሎች መሻሻያዎች ይደረጉለታል ተብሎ እንደሚታሰብ ነው ዘገባው የሚያመላክተው።

ምንጭ፦ bbc.com

የተተረጎመውና የተጫነው፦ በእንቻለው ታደሰ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *