የስነፈለክ ባለሙያዎች በጁፒተር ዙሪያ አስር አዲስ ጨረቃዎችን አገኙ

Home of best apps

የስነፈለክ ባለሙያዎች በጁፒተር ዙሪያ አስር አዲስ ጨረቃዎችን አገኙ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ፣11፣2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የስነፈለክ ተመራማሪዎች በትልቋ ፕላኔት ጁፒተር ዙሪያ አስር አዳዲስ ፕላኔቶችን ማግኘታቸውን አስታወቁ፡፡

በዩናይትድ ስቴትስ መረጃው ይፋ ሲሆን ጁፒተር በጥቅሉ 79 ጨረቃዎች ያሏት ፕላኔት መሆኗን ነው ተመራማሪዎቹ የገለጹት፡፡

በዚህም ጁፒተር ከየትኛውም ፕላኔት በመላቅ በምህዋሩ ውስጥ ብዙ ጨረቃ ያላት ፕላኔት መሆኗ ተረጋግጧል፡፡

አሁን አዲስ የተገኙት ጨረቃዎች ከሌሎቹ አንጻር በመጠን ትንንሽ መሆናቸው ተነግሮዋል፡፡

ጁፒተር ከፀሐይ አንጻር አምስተኛዋ ፕላኔት ስትሆን ዲያሜትሯም 142 ሺህ 984 ኪሎሜትር ነው ተብሏል፡፡

ሆኖም ከጨረቃዎቹ ጋር አንድ የተለየ ነገር ማግኘታቸውንም የገለጹ ሲሆን በዙሪያዋ ከሚሽከረከሩ ሌሎች ሳተላይቶች ጋር ልትጋጭ ትችላለች ብለዋል፡፡

ምንጭ፥ አልጄዚራ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *