‘ኢትዮ-ስፔስ’ የተባለ አዲስ የስማርት ስልክ መተግበሪያ ተሰራ

Home of best apps

‘ኢትዮ-ስፔስ’ የተባለ አዲስ የስማርት ስልክ መተግበሪያ ተሰራ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 22፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮ-ስፔስ የተባለ አዲስ የስማርት ስልክ መተግበሪያ መሰራቱ ተገለፀ።

በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የተሰራው መተግበሪያው በዚህ ወር ይፋ እንደሚደረግም ታውቋል።

አዲሱ መተግበሪያ ተቋሙን ለኀብረተሰቡ ለማስተዋወቅና ኀብረተሰቡ ስለ ስፔስ ሳይንሱ ያለው ግንዛቤ እንዲያድግ ያግዛል ተብሏል።

መተግበሪያው በኢኒስቲቲዩቱ የስፔስ ሳይንስና አፕልኬሽን የስራ ክፍል ረዳት ተመራማሪ በአቶ ዳዊት ካሱ የተሰራ መሆኑም ተገልጿል።

ኢትዮ-ስፔስመተግበሪያ ስለ ኢንስቲትዩቱ መረጃ የሚሰጥ፣ ስፔስን የተመለከተ የህጻናት መጫወቻ (ጌም)፣ የተቋሙ ዜናዎችና ስለ ስፔስ እውነታዎች እንዲሁም የአየር ንብረት ትንበያና የዓለም የስፔስ ዜናዎችን የሚያሳዩ ክፍሎች እንዳሉትም አቶ ዳዊትገልጸዋል።

በመተግበሪያው ውስጥ የተካተቱ የስፔስ እውነታዎች፣ ተቋሙን የሚያስተዋውቁ መረጃዎችና የህፃናት ጌሞች የኢንተርኔት አገልግሎት የማያስፈልጋቸው ሲሆኑ፥ የአየር ንብረት ትንበያና የዓለም የስፔስ ዜናዎች የኢንተርኔት አገልግሎት የሚፈልጉ ናቸው።

የሞባይል መተግበሪያው በኢንስቲትዩቱ ድረ-ገፅና በ’ጎግል አፕስ’ ላይ እንደሚጫንም ተናግረዋል ረዳት ተመራማሪው።

የሞባይል መተግበሪያው የመጀመሪያ ስሪት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተሰራ መሆኑን ገልጸው፥ ሁለተኛው ስሪት የአገሪቷን ቋንቋዎችና ሌሎች መተግበሪያዎችን ያካተተ እንደሚሆንም ተናግሯል።

የስራ ክፍሉ አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ የማነ በበኩሉ የሞባይል መተግበሪያው ስራ መጠናቀቁንና በዚህ ወር ይፋ ተደርጎ ለኀብረተሰቡ ተደራሽ እንደሚሆንም ገልጸዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *