በሀገሪቱ 15 የቴክኖሎጂ ድጋፍ የሚያደርጉ ማዕከላት ሊገነቡ ነው፥ የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት

Home of best apps

በሀገሪቱ 15 የቴክኖሎጂ ድጋፍ የሚያደርጉ ማዕከላት ሊገነቡ ነው፥ የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2010፣ (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት 15 የቴክኖሎጂ ፈጠራ ድጋፍ የሚያደርጉ ማዕከላት እንዲገነቡ የማድረግ እቅድ እንዳለው ገልጿል።

ቀደም ሲል በ6 ተቋማት ማዕከላቱ እንደተከፈቱ የተገለጸ ሲሆን ፥ 15 ዩኒቨርሲቲዎች እና የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆችም የቴክኖሎጂ ፈጠራ ድጋፍ ማዕከላትን ለማቋቋም ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት ጋር እንደተፈራረሙ ታውቋል።

በማዕከላቱ የአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ጊዜያቸው ያለፈባቸውን የፈጠራ ስራዎች ተሰባስበው እንደሚቀመጡም ተገልጿል።

ማዕከላቱ የፈጠራ ስራዎችን ለመቅዳት፣ ለማሻሻልና ለማላመድ የሚያስችሉ መረጃዎች እንዲደራጁ ለማድረግ ያስችላሉ ነው የተባለው።

እስካሁን 13ሚሊየን የፈጠራ መብት ፈቃድ መረጃዎች በየተቋማቱ መሰራጨታቸውን የገለጹት
የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ፅ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ኤርሚያስ የማነብርሃን ምን ያህሉ መረጃዎች ጥቅም ላይ እንደዋሉም የዳሰሳ ጥናት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

በፈጠራው ሂደት ጊዜና ጉልበትን ከማባከን ይልቅ የአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ጊዜያቸው ያለፈባቸውን የቴክኖሎጂና የፈጠራ ስራዎችን በመቅዳት፣ በማሻሻልና በማላመድ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነውም ተብሏል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *