ጎግል የአንድሮይድ የጽሁፍ መልእክት መለዋወጫ ኤስ.ኤም.ኤስ አገልግሎትን ሊቀይር ነው

Home of best apps

ጎግል የአንድሮይድ የጽሁፍ መልእክት መለዋወጫ ኤስ.ኤም.ኤስ አገልግሎትን ሊቀይር ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 15፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጎግል በአንድሮይድ ስማርት ስልኮች ላይ አጭር የጽሁፍ መልእክት መለዋወጫ ኤስ.ኤም.ኤስ አገልግሎትን በሌላ ሊተካ መሆኑ ተሰምቷል።

ጎግል የጽሁፍ መልእክት መለዋወጫ (ኤስ.ኤም.ኤስ) አገልግሎቱን “ቻት” በሚባል አዲስ አገልግሎት የሚቀይር ሲሆን፥ አዲሱን መገልገያ በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ አንድሮይድ ስማርት ስልኮች ለመልቀቅ ዝግጅት ማጠናቀቁን ተገልጿል።

ጎግል አገልግሎቱን በይፋ ለተጠቃሚዎች ሲያቀርብም አሁን የምንጠቀምበት የአጭር ጽሁፍ መልእክት መለዋወጫ (SMS) ሙሉ በሙሉ በቻት ተሚተካ ይሆናል።

ቻት የተባለው አዲሱ አገልግሎትም ከዚህ በፊት በአንድሮይድ ስልኮች የመልእክት መለዋወጫ አገልግሎት ላይ ያልነበሩ አዳዲስ ነገሮችን ይዞ መምጣቱ ታውቋል።

ከእነዚህም መውስጥ በቡድን መልእክት መላላክ፣ የቪዲዮና የድምፅ መልእክት መላላክ እና ሌሎች የአጭር ጽሁፍ መልእክት መለዋወጫ (SMS) አገልግሎት ውስጥ ያልነበሩ አዳዲስ መገልገያዎችን ይገኙበታል።

ሆኖም ግን በአዲሱ የመልእክት መለዋወጫ ቻት በኩል ሁሉንም አገልግሎቶች መጠቀም የሚቻለው የየሀገራቱ የኔትዎርቅ አቅራቢ ድርጅቶች አሰራር መሰረት ነው ተብሏል።

ይህ ማለትም በመልእክት መለዋወጫ በኩል የቪዲዮ መልእክትን መላላክን የማይፈቅድ የኔት ዎርክ አቅራቢ ካለ እዛ አካባቢ ያሉ ሰዎች አገልግሎቱን መጠቀም አይችሉም።

ጎግል ቻት የተባለውን አዲሱን የመልእክት መለዋወጫ አገልግሎቱን ይፋ ለማድረግ ከ50 በላይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ ቆይቷል የተባለ ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ ቮዳፎን፣ ሳምሰንግ፣ ኤል ጂ፣ ቲ ሞባይል፣ ቬራይዘን እና ሁዋዌይ ይገኙበታል።

ምንጭ፦ www.bbc.com

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *