በኦንላይን 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ፋይሎች በበይነ-መረብ አጠቃቀም ጉድለት ምክንያት ለመረጃ መንታፊዎች ተጋልጠው ይግኛሉ-ተመራማሪዎች

Home of best apps

በኦንላይን 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ፋይሎች በበይነ-መረብ አጠቃቀም ጉድለት ምክንያት ለመረጃ መንታፊዎች ተጋልጠው ይግኛሉ-ተመራማሪዎች

አዲስ አበባ ሚያዚያ 05፣ 2010፣ (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዓለም አቀፍ ደረጃ በኦንላይን የሚገኙ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ያህል የክፍያ ደረሰኞች፣ የህክም ፋይሎች እና የህሙማን መረጃ መቀበያ ፎርሞች በቀላሉ በ3ኛ ወገን እጅ ሊገቡ የሚችሉበት ደረጃ ላይ እንደሆኑ ተመራማሪዎች ገልጸዋል።

ዲጂታል ሻዶው የተባለው ኩባንያ የሳይበር ደህንነት ተመራማሪዎች በዘርፉ ላይ ለ3 ወር ባካሄዱት ጥናት 700 ሺህ የክፍያ ደረሰኞች፣ 60 ሺህ የወጪና ገቢ ደረሰኞች እና 2 ነጥብ 2 ሚሊየን የጤና ፋይሎች በዓለም አቀፍ ደረጃ በበይነ-መረብ ልውውጥ ሂደት ላይ ያሉና በቀላሉ በሶስተኛ ወገን እጅ ለመግባት የሚያስችላቸው ሁኔታ ላይ መሆናቸውን አረጋግጠዋል ተብሏል።

የድርጅቶች መረጃዎች፣ የፈጠራ ስራዎችና የፈጠራ መብት ማስረጃዎችም በዚህ መረጃ ውስጥ እንደተካተቱም ታውቋል።

የዲጅታል ሻዶው ኩባንያ ምክትል ስራ አስኪያጅ ሬክ ሆላንድ እንደገለፁት፥ ፋይሎቹ በቀላሉ ለመረጃ በርባሪዎች በቀላሉ ሊጋለጡ የሚችሉበት ሁኔታ ላይ ናቸው።

በበይነ-መረብ አጠቃቀም ጉድለት በህይወታችን ላይ ወሳኝ የሆኑ መረጃዎችን በተቀናቃኝ ሀገራት መረጃ በርባሪዎች ወይንም በተወዳዳሪ ኩባንያዎች ልናጣቸው የምንችል እንደሆነ ነው ስራ አስኪያጁ የሚያስረዱት።

የመረጃ በርባሪዎች ጉዳይ በዓለም አቀፍ ደረጃ አሳሳቢ በሆነበት ጊዜ እንኳ የበይነ-መረብ ተጠቃሚዎቹ መረጃቸውን ከውጭ ጥቃት ለመጠበቅ ትኩረት የሌላቸው መሆኑን ነው ዘገባው የሚያሰረዳው።

ከመረጃ ቋት፣ ፋይሎችን ከምንቀያየርባቸው መንገዶችና ፋይሎችን አገልግሎት ከምናውልበት ጉዳይ ጋር በተያያዙ ክፍተቶች ችግሩ እንደሚከሰትም ተጠቁሟል።

ከዚህም ሌላ ከእውቀት እጥረትና አጠቃቀም ጉድለት ጋር በተያያዘ እያንዳንዱ የበይነ- መረብ ተጠቃሚ መረጃዎችን ለመረጃ በርባሪዎች እንደሚያጋልጥም ነው የተገለጸው።

በዚህም የፋይል ደህንነቶቻችንን ያለመጠበቅ፣ የሰርቨር እና ፋይሎችን የምንቀባበልበት መንገድ ጉድለት በርካታ ግላዊ መረጃዎች በመረጃ በርባሪዎች እጅ እንዲወድቁ የሚያደረጉ እንደሆነ ታይቷል።

ምንጭ፦ fossbytes.com

የተተረጎመና የተጫነው፦ እነቻለው ታደሰ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *