NEWS

Home of best apps

የደም ምርመራና ትንተና መረጃዎችን ለመስራት የሚያስችል ሮቦት መስራታቸውን ተመራማሪዎቹ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደም ምርመራና መረጃዎቸን ትንተና ለመስራት የሚያስችል ሮቦት መስራታቸውን ተመራማሪዎቹ ገልጸዋል። በሩትገርስ ዩንቨርስቲ ተመራማሪዎች የተሰራው አዲሱ ሮቦት ትክክለኛና ወቅታዊ የደም ምርመራ ውጤትና ትንተና መረጃ በመስጠት የዘርፉን ባለሙያዎችና ህሙማን ያግዛል ተብሏል። ቴክኖሎጂው በተገጠመለት ካሜራ የሰዎቹን እጅ ስካን በማድረግ በቀላሉ የደም ስሮችን በመለየት ቀደም ሲል ባለሙያዎች በመርፌ በመሰርሰር የደም ስሮችን ይፈልጉ የነበረውን…
Read more

ስፔስ ኤክስ እጅግ ትልቅ አቅም ያለው ወታደራዊ ሮኬት አመጠቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2010 (ኤፍቢሲ) በዩናይትድ ስቴትስ ስፔስ ኤክስ የተሰኘው የግል ኩባንያ በዓለም ላይ እጅግ ትልቅ አቅም ያለው ሮኬት ማምጠቁን አስታወቀ፡፡ ፋልከን ሄቪይ በመባል የሚታወቀው ይህ ሮኬት በፍሎሪዳ ግዛት በሚገኘው ከኬኔዲ የህዋ ማዕከል መነሳቱ ተነግሯል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ አየር ኃይል እንዳስታወቀው ፋልከን ወደ ህዋ የተላከው ሚስጥራዊ ለሆነ ወታደራዊ ተልእኮ መሆኑን አስታውቋል፡፡ አየር ኃይሉ አሁን ያመጠቀው ሳተላይት…
Read more

ጎግል የበይነ መረብ አገልግሎት ሳይኖር መረጃዎችን ለመጠቀም የሚያስችል መተግበሪያ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ18፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጎግል የበይነ መረብ አገልግሎት ሳይኖር መረጃዎችን ለመጠቀም የሚያስችል መተግበሪያ ይፋ ማድረጉ ተገልጿል። መተግበሪያው የሞባይል ኔት ወርክ የማስፋፋት ውስንነት ባለባቸውና የበይነ መረብ መቆራረጥ ችግር የሚያጋጥማቸው አካባቢዎችን ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀ ነው ተብሏል።  ቴክኖሎጂው በተለያዩ አካባቢዎች ተፈላጊነት ያላቸውን አርቲክሎች እየመረጠ የበይነ መረብ አገልግሎት በማይኖርበት ጊዜ ለማንበብ እንደሚያስችል ነው የተገለጸው። ከዚህም ሌላ ደንበኞቹ ወደ…
Read more

ፌስ ቡክ ደንበኞቹ የሰዓት አጠቃቀማቸውን ለመቆጣጠር የሚያስችል መተግበሪያ አገለግሎት ላይ ሊያውል ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ18፣20110 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፌስ ቡክ ደንበኞቹ የሰዓት አጠቃቀማቸውን ለመቆጣጠር የሚያስችል መተግበሪያ አገልግሎት ላይ ሊያውል መሆኑን ገልጿል። መተግበሪያው የፌስቡክ ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በእየቀኑ ምን ያህል ጊዜ እንደሚጠቀሙ መረጃ የሚሰጥ ሲሆን፥ ተጠቃሚዎቹ በእየቀኑ ለመጠቀም የሚፈልጉትን ጊዜ ለመወሰን፣ ለማስታወስና አማራጭን ለማስተካከል ያስችላል ተብሏል።  በባለፈው ዓመትም ኩባንያው ደንበኞቹ የጊዜ ገደብ በማስቀመጥ ለህዎታቸው ገንቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንዲያደረጉ…
Read more

ዋትስአፕ በቅርቡ በተወሰኑ የእጅ ስልኮች ላይ አገልግሎቱን ያቋርጣል

አዲስ አባባ፣ ሰኔ 19፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዋትስአፕ በቅርቡ በተወሰኑ የእጅ ስልኮች ላይ አገልግሎቱን እንደሚያቋርጥ ተገልጿል። አገልግሎቱ የሚያቋርጠው መተግበሪያው እየተሻሻለ ሲሄድ በተወሰኑ ስልኮች ላይ አገልግሎቱን ለማግኘት ባለመቻሉ ነው ተብሏል።  ወደ ፊት ኩባንያው አገልግሎት ላይ ለማዋል በእቅድ የያዘው መተግበሪያም በተወሰኑ አይፎኖችና አንደሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች ለመጠቀም የማይቻል መሆኑ ተገልጿል። ወደፊት አገልግሎት ላይ የሚውለውን የዋትስአፕ መተግበሪያ ለመጠቀም የሚያስችለው የአንድሮይድ…
Read more

በአውሮፓ የአሜሪካ የዜና ድረ ገጾች ተደራሽ እየሆኑ አይደለም ተባለ

አዲስ አባባ፣ ሰኔ 19፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአውሮፓ የተወሰኑ የአሜሪካ የዜና ድረ ገጾች ተደራሽ እየሆኑ እንዳልሆነ ተገልጿል። የአሜሪካ ታዋቂ የሆኑት ሎስአንጀለስ ታይምስ ና ኒውዮርክ ዲያሊ ኒውስን ጨምሮ የተለያዩ የዜና ድረ ገጾች በአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ተደራሲያን ዘንድ ተደራሽ እየሆኑ እንዳልሆነ ነው የተገለጸው። በድረ ገጹ ላይ እገዳው የተጣለው በአውሮፓ ህብራት አባል ሀገራት ላይ አዲሱ የመረጃ ጥበቃ ህግ…
Read more

ፈጣኑ የቻይና ባቡር የመጀመሪያ ጉዞውን አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ25፣2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፈጣኑ የቻይና ባቡር የመጀመሪያ ጉዞውን በቤጂንግ የባቡር መስመር ላይ ማድረጉ ተገልጿል። በቤጂንግ ከተማ የመጀመሪያ ጉዞውን ያደረገው ይህ ባቡር በሰዓት 350 ኪ/ሜትር የሚጓዝ ሲሆን፥ 400 ሜትር ርዝመትና 16 ተጎታጆች አሉት ተብሏል።  ባቡሩ አሁን ላይ በሀገሪቱ አገልግሎት ላይ ካሉት ባቡሮች የ2 እጥፍ ብልጫ ያለውና 1ሺህ200 መንገደኞችን በአንድ ጊዜ ለማጓጓዝ እንደሚያስችልም ነው የተገለጸው። ጂ…
Read more

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ ከሮቦቷ ሶፍያ ጋር ቆይታ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሶፍያ ከተባለችው ሮቦት ጋር በዛሬው እለት ቆይታ አድርገዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአይ.ሲ.ቲ ኤክስፖ ኢትዮጵያ 2010 ላይ የተገኘችውን ሮቦቷን ሲፊያ ነው በዛሬው እለት ያገኙት። ሶፊያ የተባለችው ሮቦት 67 በመቶ ፕሮግራም የተደረገችው እና የተሰራቸው በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ነው። በዚህ ወቅትም ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ…
Read more

ትዊተር በእስራኤል የሃማስና የሂዝቦላ የትዊተር አድራሻዎችን ዘጋ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 26 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ግዙፉ የማህበራዊ ትስስር ሚዲያ ትዊተር በእስራኤል አገልግሎት የሚሰጡ የሃማስና የሂዝቦላ የትዊተር አድራሻዎችን ዘግቷል። ኩባንያው እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የእስራኤል መንግስት ለኩባንያው ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ነው ተብሏል። የእስራኤል መንግስት በእስራኤል አገልግሎት የሚሰጡ የሁለቱ ቡድኖች የትዊተር አድራሻዎች ስጋት ሆነዋል ሲል ለኩባንያው አስታውቋል። የእስራኤል የሃገር ውስጥ የደህንነት ሚኒስትር…
Read more

በሰከንድ 490 ሜጋ ባይት ፋይልን ለመላላክ የሚያስችለው ፈጣኑ የጎግል ጎ መተግበሪያ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጎግል ያለኢንተርኔት መረጃን ለመላላክ የሚያስችለው ጎ መተግበሪያው ላይ ማሻሻያ ማድረጉ ተነግሯል። ጎግል ጎ የተባለውን መተግበሪያውን ባሳለፍነው ዓመት ያስተዋወቀ ሲሆን፥ መተግበሪያውም የአንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም በሚጠቀሙ ስልኮች ላይ ነው የሚሰራው። መተግበሪያው በስልካችን ላይ ያሉንን መረጃዎች አስተካክለን ለመያዝ የሚረዳ ሲሆን፥ ያለኢንተርኔት ግንኙነትም በተወሰነ ክልል ውስጥ ላሉ ስልኮች የተለያዩ መረጃዎችን ለመላላክ ያገለግላል። በተጨማሪም…
Read more

ዘጠኝ ካሜራዎች ያሉት ስልክ ተዘጋጀ

አዲስ አበባ፣ሰኔ፣ 27፣2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ላይት ዘጠኝ ካሜራዎች ያሉት ስልክ ማዘጋጀቱን አስታወቀ። ከዚህ በፊት ጋላክሲ ኤስ9 ፕላስና ሁዋዊ ፒ20 ፕሮ ሁለትና ሶስት የኋላ ካሜራ ያለው ስልክ ማዘጋጀታቸው ይታወሳል። የካሜራ አምራች የሆነው ላይት ዘጠኝ የኋላ ካሜራ ያሉት ስልክ እያዘጋጀ እንደሆነ ነው ያስታወቀው። ይህ ዘጠኝ ካሜራዎች ያሉት ስልክ በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት ለገበያ እንደሚቀርብ ነው የሚጠበቀው። ይህ ካሜራ ከተለያዩ…
Read more

ትዊተር በ2 ወራት ውስጥ የ70 ሚሊየን ደንበኞች አገልግሎትን አቋረጠ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 02፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ትዊተር በ2 ወራት ውስጥ ከ70 ሚሊየን በላይ ደንበኞቹን አገልግሎት ማቋረጡ ተገልጿል። ኩባንያው የደንበኞቹን አገልግሎት ያቋረጠው በማህበራዊ ሚዲያው የሚዘዋወሩ የተዛቡ መረጃዎችን ለመቀነስ መሆኑም ታውቋል። ትዊተር 336 ሚሊየን ያህል ደንበኞች ያሉት ሲሆን፥ ከነዚህም መካከል ከ70 ሚሊየን ያህል በላይ ደንበኞች በመረጃ አጠቃቀማቸው ላይ ችግሮች መታየታቸውና አገልግሎታቸው መቋረጡ ነው የተገለጸው። በዚህም ባለፉት 2…
Read more