Category: Uncategorized

Home of best apps

ተስላ ኩባንያ በዓመት 500 ሺህ ተሽከርካሪዎቸን ማምረት የሚችል ፋብሪካ በሻንጋይ ሊከፍት ነው

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ03፣2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ተስላ የተባለው ተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ በዓመት 500 ሺህ ተሽከርካሪዎቸን ማምረት የሚችል ፋብሪካ በቻይናዋ ከተማ ሻንጋይ ሊከፍት ነው ተብላል። ኩባንያው ከሻንጋይ ከተማ አስተዳደር ባለስልጣናት ጋር ሊንጋንግ በተባለው አካባቢ የተሽከርካሪ ፋብሪካውን ለመገንባት መፈራረሙም ታውቋል። ኩባንያው በቻይና ፋብሪካውን ለመክፈት ያቀደው በኤለክትረክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች በቻይና ሰፊ ገበያ እንዳላቸው በማረጋገጥና አሁን ላይ አሜሪካ ወደ ቻይና የሚገቡ…
Read more

ካስፐርስኪ በአውሮፓ የሚያደርገውን የሳይበር ወንጀል የመከላከል ስራ አቋረጠ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ካስፐርስኪ የተባለው የኮምፒውተር ደህንነት ተቋም ከአውሮፓ ተቋማት ጋር በመሆን የሚያከናውነውን የሳይበር ወንጀል መከላከል ስራ ማቋረጡን አስታውቋል። ኩባንያው ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ የካስፐርስኪ ሶፍትዌር ተአማኒነት ይጎድለዋል በሚል ያቀረበውን ሞሽን ለመዋቀም መሆኑ ተነግሯል። ካስፐርስኪ ኩባንያ፥ የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ያቀረበበት ውንጀላ ከእውነት የራቀ እና የኩባንያውን ክብር የማይመጥን ነው ብሎታል።…
Read more

ፌስ ቡክ ከመረጃ ብርበራ ጋር በተያያዘ ጉዳይ ለደንበኞቹ የካሳ ክፍያ እንደማይፈጽም ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት17፣2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፌስ ቡክ ካምብሪጅ አናሊይቲካ በደንበኞቹ ላይ አደረሰ ከተባለው የመረጃ ብርበራ ጋር በተያያዘ ጉዳይ የካሳ ክፍያ እንደማይከፍል አስታውቋል። ኩባንያው ለደንበኞቹ የካሳ ክፍያ የማይፈጽም መሆኑን የገለጸው ከዚህ ሳምንት በፊት በብራሰልስ የአውሮፓ ህብረት ህግ አውጪዎች ለኩባንያው ዋና ስራ አስኪያጅ ማርክ ዙከርበርግ የክፍያ ከሳን በተመለከተ ላቀረቡላቸው ጥያቄ በተሰጠ የጽሁ ምላሽ ነው ተብሏል። የአውሮፓ ህብረት ህግ አውጪዎች የህብረቱ ሀገራት…
Read more

ተመራማሪዎች ያለገደብ መልሶ ጥቅም ላይ የሚውል አዲስ ፕላስቲክ ሰሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 22፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተመራማሪዎች ቡድን በአይነቱ አዲስ የሆነ ፕላስቲክ መስራታቸው ተነግሯል። የኮለራዶ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች የሰሩት አዲሱ ፕላስቲክ በመልሶ ጥቅም ላይ ማዋል ዘዴ ያለ ገደብ በድግግሞሽ በማምረት ለመጠቀም የሚያስችል ነው። በዩኒቨርሲቲው የኬሚስትሪ ትምህርት ክፍል ፕሮፌሰር ኢዩጂን ቼን እንደሚናገሩት፥ አዲሱ ግኝት በየዓመቱ የምንጥለውን የፕላስቲክ ቆሻሻ መጠን ለመቀነስ አይነተኛ መፍትሄ ነው ብለዋል። በየዓመቱ 12…
Read more

ኤች.ፒ ለመረጃ ጠላፊዎች 10 ሺህ ዶላር ሊሸልም መሆኑ ተነግሯል

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 30፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኤች.ፒ የተባለው የቴክኖሎጂ ቁሶች አምራች ኩባንያ በማተሚያ ማሽን (ፕሪንተር) ምርቱን በመጥለፍ ክፍተቱን ለሚያመላክቱ የመረጃ ጠላፊዎች 10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ሊሸልም መሆኑ ተነግሯል። በዚህም ኤች ፒ ኩባንያ የፕሪንተር ምርቶችን ለሚጠልፉ የመረጃ በርባሪዎች ዳጎስ ያለ የገንዘብ ሽልማት ያቀረበ የመጀመሪያው ኩባንያ መሆን ችሏል ነው የተባለው። እንደ ኤች ፒ ገለፃ፥ ኩባንያው በፕሪንተር ምርቱ…
Read more

ቻይናውያን ተመራማሪዎች የጨረር መሳሪያ መስራታቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 3 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይናውያን ተመራማሪዎች የጨረር መሳሪያ መስራታቸውን እየገለጹ ነው። ማንነታቸው ያልተገለጸው ተመራማሪዎች ኢላማውን ከረጅም ርቀት የሚመታ የጨረር መሳሪያ መስራታቸውን ገልጸዋል። ዜድ ኬ ዜድ ኤም 500 የተሰኘው የጨረር መሳሪያ ከ804 ሜትር ኢላማውን መምታት እንደሚችልም ነው ተመራማሪዎቹ የገለጹት። መሳሪያው ኢላማውን ከተጠቀሰው ርቀት ላይ የሚመታ ሲሆን፥ ኢላማው ላይ ካረፈ በኋላም…
Read more

ሳምሰንግ በፈረንጆቹ 2020 ሙሉ በሙሉ ታዳሽ ሀይል እንደሚጠቀም አስታወቀ

አዲስአበባ፣ሰኔ፣ 7፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) ሳምሰንግ በአውሮፓ፣ አሜሪካና ቻይና የሚገኙ ቢሮዎች፣ ማምረቻዎችና ሌሎች መሳሪያዎቹ በቀጣይ ሁለት ዓመታት የታዳሽ ሀይል እንደሚጠቀሙ አስታወቀ፡፡ ይህን ተግባራዊ ለማድረግ የዲጂታል ከተማ ዋና መስሪያ ቤቱን ወደ ፀሀይ ሀይል መሰብሰቢ በመቀየር ላይ የሚገኝ ሲሆን 42 ሺህ ስኩየር ሜትር የሚረዝም የፀሀይ መሰብሰቢያ ለመግጠም በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡ የፀሀይ ሀይል መሰብሰቢያው የስድስት ስታድየሞች ስፋት ያለው ነው…
Read more

አማዞን የሰዎችን ማንነት በፊት ብቻ መለየት የሚያስችለውን መሳሪያ ለገበያ እንዳያቀርብ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች አሳሰቡ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት፣ 15 2010(ኤፍቢሲ) የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የሰዎችን ማንነት በፊት ብቻ መለየት የሚያስችለው መሳሪያ አማዞን ለመንግስት እና ሌሎች መሳሪያን ለሚፈልጉ አካላት ማቅረብ እንደሌለበት አሳሰቡ። ተሟጋቾቹ ይህ መሳሪያ በስደተኞች እና በቆዳ ቀለም ምክንያት ሰዎች ተፅዕኖ እንደሚደርስባቸው የሚያደርግ በመሆኑ ተግባራዊ መሆን የለበትም ብለዋል። ከ40 በላይ የሚሆኑት የመብት ተሟጋቾች ለአማዞን የኦንላይን ገበያ ስፍራ ባለቤት ለሆኑት ጆፍ ቤዞስ…
Read more

የመረጃ መረብ ጠላፊዎች በሚሊየን የሚቆጠሩ የሆቴል ክፍሎችን የሚከፍት ቁልፍ መስራታቸው ተነገረ

አዲስ አበባ ሚያዚያ፣ 22፣ 2010፣(ኤፍ.ቢ.ሲ) የመረጃ መረብ ጠላፊዎች ያለ አንዳች አሻራ በደቂቃዎች የዓለም ዓቀፍ ሆቴሎች ክፍሎችን በር ለመክፈት የሚያስችል ቁልፍ (ማስተር ኪ) መስራታቸውን የሳይበር ጥቃት ደህንነት ተመራማሪዎች ገለፁ። በፊንላንድ የመረጃ መረብ ደህንነት ኩባንያ የዘረፉ አማካሪ የሆኑት ቶሚ ቱሚኔንና ቲሞ ሂርቮኔን እንደገለፁት “ቪንግ ካርድ ኤልሴፍ” የተባለ ዘመናዊ የሆቴሎች የኤሌክትሮኒክስ ቁልፎች ላይ ሶፍትዌር ላይ ጥቃት መፈጸሙ ተረጋግጧል።…
Read more

የቻይናው ዲዲ ኩባንያ የተሽከርካሪ አገልግሎቱን ለማዘመን የ1ቢሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 30፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቻይናው ዲዲ ኩባንያ የተሽከርካሪ አገልግሎቱን ለማዘመን የ1ቢሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት ይፋ አድርጓል። በቻይና የተሽከርካሪ አገለግሎት ላይ የተሰማራው ዲዲ ኩባንያ አገልግሎቱን ለማዘመንና የንግድ ምልክቱን ለማደስ የአንድ ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ኢንቨስትመን ይፋ አድርጓል።  ኩባንያው የተሽከርካሪ ሊዝ ሽያጭ፣ ጥገና እና የጋዝ ማደያ አገልግሎት ላይ የተሰማራ ሲሆን፥ ዓመታዊ የአገልግሎት ገቢው 8 ነጥብ 79 ቢሊየን…
Read more

ትዊተር በ2 ወራት ውስጥ የ70 ሚሊየን ደንበኞች አገልግሎትን አቋረጠ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 02፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ትዊተር በ2 ወራት ውስጥ ከ70 ሚሊየን በላይ ደንበኞቹን አገልግሎት ማቋረጡ ተገልጿል። ኩባንያው የደንበኞቹን አገልግሎት ያቋረጠው በማህበራዊ ሚዲያው የሚዘዋወሩ የተዛቡ መረጃዎችን ለመቀነስ መሆኑም ታውቋል። ትዊተር 336 ሚሊየን ያህል ደንበኞች ያሉት ሲሆን፥ ከነዚህም መካከል ከ70 ሚሊየን ያህል በላይ ደንበኞች በመረጃ አጠቃቀማቸው ላይ ችግሮች መታየታቸውና አገልግሎታቸው መቋረጡ ነው የተገለጸው። በዚህም ባለፉት 2…
Read more

አሜሪካ የዓለም ፈጣኑንና ትልቁን ኮምፒተር ይፋ አድርጋለች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ5፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አሜሪካ የዓለም ፈጣኑንና ትልቁን ኮምፒተር ይፋ ማድረጓ ተገልጿል። በዘርፉ በቻይና ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን በማሻሻል የዓለም ፈጣኑንና ትልቁን ኮንፒተር አገልግሎት ላይ ማዋሉን የአሜሪካው ዓለም አቀፍ የማሽን ንግድ ኮርፖረሽን ባሳለፍነው አርብ ይፋ ማድረጉ ተገልጿል።  ሳሚት የሚል ስያሜ የተሰጠው ይኼው ፈጣኑና ትልቁ ኮምፒዩተር አሁን ላይ አሜሪካ ተንሴ ውስጥ ኦካክ ሪጅ ብሄራዊ ቤተሙከራ…
Read more