Tag: ሌሎች ዜናዎች:

Home of best apps

ማይክሮ ሶፍት ኩባንያ የምርጫ ሂደትን ከመረጃ መንታፊዎች የሚታደግ ቴክኖሎጂውን ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ ሚያዚያ 8፣ 2010፣ (ኤፍ.ቢ.ሲ) የበይነ መርብ መስፋፋት መረጃዎችን ከምንግዜውም የበለጠ ለመረጃ መንታፊዎች ተጋላጭ ያደረጋቸው ሲሆን፥ ሰዎቹ የምርጫ ሂደትን የመሰሉ መሰረታዊ ጉዳዮችን ከእነዚህ የመረጃ መንታፊዎቹ የመጠበቅ ጉዳይ አሳሳቢ አድርጎታል።  በ2016 የአሜሪካ የምርጫ ሂደት ላይ ሩሲያ ተጫወተችው የተባለው ሚናም በአብዛኛዎቹ ዘንድ የሚታወስ ነው።  በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆነው የማይክሮ ሶፍት ኩባንያ የአሜሪካን ጉዳይ ብቻ ሳይሆን…
Read more

ጎግል የአንድሮይድ የጽሁፍ መልእክት መለዋወጫ ኤስ.ኤም.ኤስ አገልግሎትን ሊቀይር ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 15፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጎግል በአንድሮይድ ስማርት ስልኮች ላይ አጭር የጽሁፍ መልእክት መለዋወጫ ኤስ.ኤም.ኤስ አገልግሎትን በሌላ ሊተካ መሆኑ ተሰምቷል። ጎግል የጽሁፍ መልእክት መለዋወጫ (ኤስ.ኤም.ኤስ) አገልግሎቱን “ቻት” በሚባል አዲስ አገልግሎት የሚቀይር ሲሆን፥ አዲሱን መገልገያ በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ አንድሮይድ ስማርት ስልኮች ለመልቀቅ ዝግጅት ማጠናቀቁን ተገልጿል። ጎግል አገልግሎቱን በይፋ ለተጠቃሚዎች ሲያቀርብም አሁን የምንጠቀምበት የአጭር ጽሁፍ መልእክት…
Read more

በሀገሪቱ 15 የቴክኖሎጂ ድጋፍ የሚያደርጉ ማዕከላት ሊገነቡ ነው፥ የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2010፣ (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት 15 የቴክኖሎጂ ፈጠራ ድጋፍ የሚያደርጉ ማዕከላት እንዲገነቡ የማድረግ እቅድ እንዳለው ገልጿል። ቀደም ሲል በ6 ተቋማት ማዕከላቱ እንደተከፈቱ የተገለጸ ሲሆን ፥ 15 ዩኒቨርሲቲዎች እና የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆችም የቴክኖሎጂ ፈጠራ ድጋፍ ማዕከላትን ለማቋቋም ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት ጋር እንደተፈራረሙ ታውቋል። በማዕከላቱ የአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ጊዜያቸው ያለፈባቸውን የፈጠራ…
Read more

ዩ ቲዩብ አላስፈላጊ ይዘት ያላቸውን 8 ነጥብ 3 ሚሊየን ተንቀሳቃሽ ምስሎችን አስወገደ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 16 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ዩ ቲዩብ ባለፈው የፈረንጆቹ አመት አላስፈላጊ ይዘት ያላቸውን 8 ነጥብ 3 ሚሊየን ተንቀሳቃሽ ምስሎች ማጥፋቱን አስታወቀ። ኩባንያው በፈረንጆቹ 2017 ሶስተኛ ሩብ አመት የስራ አፈጻጸሙን የተመለከተ ሪፖርት አውጥቷል። በሪፖርቱ ላይም ከጥቅምት እስከ ታህሳስ ወር ድረስ የኩባንያውን ህግና ደንብ የተላለፉ ተንቀሳቃሽ ምስሎች (ቪዲዮ) ማጥፋቱን ነው ያስታወቀው። ለዚህ…
Read more

በቻይና የመጀመሪያው አሽከርካሪ አልባ አውቶቡስ ለእይታ ቀርቧል

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 16 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና የመጀመሪያው አሽከርካሪ አልባ አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ለእይታ ቀርቧል። አውቶቡሱ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን፥ ፉጂያን ግዛት መዲና በሆነችው ፉዡ ከተማ በተዘጋጀ አውደ ርዕይ ላይ ነው ለእይታ የቀረበው። ዛሬ በሚጠናቀቀው አውደ ርዕይ ላይ በሚኖረው ቆይታም አውቶቡሱ እስከ 1 ሺህ የሚደርሱ መንገደኞችን ያጓጉዛል ተብሎ ይጠበቃል። አውቶቡሱ…
Read more

አንጎላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደህዋ ያመጠቀቻት ሳተላይት ስራ አቆመች

አዲስአበባ፣ ሚያዚያ 16፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) አንጎላ በሩሲያ እርዳታ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ህዋ ያመጠቀቻት ሳተላይት ስራ ማቆሟን አስታወቀች። አንጎሳት 1 በመባል የምትጠራው ሳተላይት ከካዛኪስታን ጣቢያ ወደ ህዋ የተላከችው ከአራት ወራት በፊት ነበር። 300 ሜትር ያህል የምትረዝመው ይህች ሳተላይት ወደ ህዋ የተላከችው ለመገናኛ አገልግሎት ለማዋል እንደነበር ተገልጿል። ሳታላይቷ የቴክኒክ እክል የገጠማት ከመጠቀች ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ሲሆን፥…
Read more

በራሱ ጊዜ ወደ መኪናነት መቀየር የሚችል ሮቦት ተዘጋጀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 18፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጃፓን ኢንጅነሮች ሰው መያዝ ሚችልና ወደ መኪናነት መቀየር የሚችል ሮሆቦት ማዘጋጀታቸውን ይፋ አደረጉ፡፡ በሮቦት የቴክኖሎጅ ፈጠራ ታሪክ የመጀመሪያው አስደናቂ ክስተት አንደሆነ ነው የተነገረው፡፡ ሁለት ሰዎችን የሚይዘው እና በደቂቃ ውስጥ ወደ ስፖርት መኪናነት የሚቀየረው ይህ ሮቦት 3 ነጥብ 7 ሜትር እንደሚረዝም ተነገሯል፡፡ ሮቦቱን ለማዘጋጀት የህፃናት አንሜሽን ፌልም መነሻ እንደሆናቸው አዘጋጆቹ…
Read more

የወረቀት ገንዘብ ከገበያ የሚወጣበት ጊዜ እየተቃረበ ይሆን?

አዲስአበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቅርብ ዓመታት ውስጥ የወረቀት ገንዘብ በኤሌክትሮኒክስ ንግድ፣ በሞባይል ክፍያና በካርድ ሊተካ እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡ ማንችስተር ከተማና በቴኔስ የተደረጉ የሙዚቃ ድግሶች ሙሉ ለሙሉ ከጥሬ ገንዘብ ውጪ መከናወናቸውን እንደምሳሌ በማንሳት የኤሌክትሮኒክስ ግብይት በቅርብ ዓመታት ግብይቱን ሊቆጣጠረው ይችላል ይላሉ፡፡ በተለያዩ ሀገራት በገበያ ስፍራዎች የኤሌክትሮኒክስ ካርድ የሚያነቡ ትንንሽ ማሽኖች ማየትም እየተለመደ መጥቷል፡፡ አንድ በዩናይትድ…
Read more

‘ኢትዮ-ስፔስ’ የተባለ አዲስ የስማርት ስልክ መተግበሪያ ተሰራ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 22፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮ-ስፔስ የተባለ አዲስ የስማርት ስልክ መተግበሪያ መሰራቱ ተገለፀ። በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የተሰራው መተግበሪያው በዚህ ወር ይፋ እንደሚደረግም ታውቋል። አዲሱ መተግበሪያ ተቋሙን ለኀብረተሰቡ ለማስተዋወቅና ኀብረተሰቡ ስለ ስፔስ ሳይንሱ ያለው ግንዛቤ እንዲያድግ ያግዛል ተብሏል። መተግበሪያው በኢኒስቲቲዩቱ የስፔስ ሳይንስና አፕልኬሽን የስራ ክፍል ረዳት ተመራማሪ በአቶ ዳዊት ካሱ የተሰራ መሆኑም ተገልጿል።…
Read more

የመረጃ መረብ ጠላፊዎች በሚሊየን የሚቆጠሩ የሆቴል ክፍሎችን የሚከፍት ቁልፍ መስራታቸው ተነገረ

አዲስ አበባ ሚያዚያ፣ 22፣ 2010፣(ኤፍ.ቢ.ሲ) የመረጃ መረብ ጠላፊዎች ያለ አንዳች አሻራ በደቂቃዎች የዓለም ዓቀፍ ሆቴሎች ክፍሎችን በር ለመክፈት የሚያስችል ቁልፍ (ማስተር ኪ) መስራታቸውን የሳይበር ጥቃት ደህንነት ተመራማሪዎች ገለፁ። በፊንላንድ የመረጃ መረብ ደህንነት ኩባንያ የዘረፉ አማካሪ የሆኑት ቶሚ ቱሚኔንና ቲሞ ሂርቮኔን እንደገለፁት “ቪንግ ካርድ ኤልሴፍ” የተባለ ዘመናዊ የሆቴሎች የኤሌክትሮኒክስ ቁልፎች ላይ ሶፍትዌር ላይ ጥቃት መፈጸሙ ተረጋግጧል።…
Read more

ተመራማሪዎች ያለገደብ መልሶ ጥቅም ላይ የሚውል አዲስ ፕላስቲክ ሰሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 22፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተመራማሪዎች ቡድን በአይነቱ አዲስ የሆነ ፕላስቲክ መስራታቸው ተነግሯል። የኮለራዶ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች የሰሩት አዲሱ ፕላስቲክ በመልሶ ጥቅም ላይ ማዋል ዘዴ ያለ ገደብ በድግግሞሽ በማምረት ለመጠቀም የሚያስችል ነው። በዩኒቨርሲቲው የኬሚስትሪ ትምህርት ክፍል ፕሮፌሰር ኢዩጂን ቼን እንደሚናገሩት፥ አዲሱ ግኝት በየዓመቱ የምንጥለውን የፕላስቲክ ቆሻሻ መጠን ለመቀነስ አይነተኛ መፍትሄ ነው ብለዋል። በየዓመቱ 12…
Read more

ቲዊተር 330 ሚሊየን ደንበኞቹ የይለፍ ቁልፎቻቸውን እንዲቀየሩ አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ፣26፣(ኤፍ.ቢ.ሲ) ቲዊተር 330 ሚሊየን ደንበኖቹ የይለፍ ቁልፎቻቸውን መቀየር እንዳለባቸው ያስጠነቀቀው የውስጥ አሰራሮቹ ላይ ችግሮች እንደገጠሙት ካረጋገጠ በኋላ ነው ተብሏል። የማህበራዊ ድረገጹ የደንበኞቹ የይለፍ ቁልፎች በሌሎች ሰዎች አገልግሎት ላይ ይዋሉ አይዋሉ ለማረጋገጥ እንዳልቻለም ነው የተገለጸው።   ኩባንያው ከጥቂት ሳምንታት በፊት ችግሩ እንደተከሰተ ያረጋገጠ ሲሆን፥ የተከሰቱ ጉድለቶችን እንዲያርሙ ለኩባንያው ሰራተኞች ሪፖርት ማድረጉም ታውቋል።  በዚህም ደንበኞቹ የይለፍ…
Read more