NEWS

Home of best apps

ቻይናውያን ተመራማሪዎች የጨረር መሳሪያ መስራታቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 3 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይናውያን ተመራማሪዎች የጨረር መሳሪያ መስራታቸውን እየገለጹ ነው። ማንነታቸው ያልተገለጸው ተመራማሪዎች ኢላማውን ከረጅም ርቀት የሚመታ የጨረር መሳሪያ መስራታቸውን ገልጸዋል። ዜድ ኬ ዜድ ኤም 500 የተሰኘው የጨረር መሳሪያ ከ804 ሜትር ኢላማውን መምታት እንደሚችልም ነው ተመራማሪዎቹ የገለጹት። መሳሪያው ኢላማውን ከተጠቀሰው ርቀት ላይ የሚመታ ሲሆን፥ ኢላማው ላይ ካረፈ በኋላም…
Read more

ተስላ ኩባንያ በዓመት 500 ሺህ ተሽከርካሪዎቸን ማምረት የሚችል ፋብሪካ በሻንጋይ ሊከፍት ነው

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ03፣2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ተስላ የተባለው ተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ በዓመት 500 ሺህ ተሽከርካሪዎቸን ማምረት የሚችል ፋብሪካ በቻይናዋ ከተማ ሻንጋይ ሊከፍት ነው ተብላል። ኩባንያው ከሻንጋይ ከተማ አስተዳደር ባለስልጣናት ጋር ሊንጋንግ በተባለው አካባቢ የተሽከርካሪ ፋብሪካውን ለመገንባት መፈራረሙም ታውቋል። ኩባንያው በቻይና ፋብሪካውን ለመክፈት ያቀደው በኤለክትረክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች በቻይና ሰፊ ገበያ እንዳላቸው በማረጋገጥና አሁን ላይ አሜሪካ ወደ ቻይና የሚገቡ…
Read more

ፌስቡክ በብሪታንያ የመረጃ ቁጥጥር ማእከል የ500 ሺህ ፓውንድ ቅጣት ተጣለበት

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የብሪታንያ የመረጃ ቁጥጥር ማእከል በፌስቡክ ላይ የ500 ሺህ ፓውንድ የገንዘብ ቅጣት ውሳኔ ማሳለፉ ተነግሯል። ማእከሉ በፌስቡክ ላይ የገንዘብ ቅጣት ውሳኔውን ያሳለፈው ኩባንያው የተጠቃሚዎቹን የግል መረጃ መጠበቅ ላይ ክፍተት አሳይቷል በሚል ነው። የኢንፎርሜሽን ኮሚሽነር ቢሮ እንዳስታወቀው፥ ፌስቡክ ካንብሪጅ አናላቲካ የሚባለው ድርጅት የተደንበኞቹን መረጃ እንዲወድስ አድርጓል፤ አሁን ደግሞ ኩባንያው መረጃውን ማጥፋቱን…
Read more

ሶፍትዌር አበልፃጊው ግለሰብ በአርቴፊሻል ኢንቴሊጀንስ ከስራው ተባረረ

አዲስ አበባ፣ሃምሌ፣4፣2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ)አርቴፊሻል ኢንቴሊጀንስ በአሁን ወቅት በባንኮች፣ ባቡር ጣቢያ፣ ሆቴል እና ሌሎች በርካታ ተቋማት ጥቅም ላይ እንደሚያውሉት ይታወቃል። በዚህም ምክንያት ወደ ፊት አርቴፊሻል ኢንቴሊጀንስ የሰውን ስራ ሙሉ በሙሉ ተከተው ሊሰሩ ይችላሉ የሚል ስጋ በበርካቶች ዘንድ ይነሳል። በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት ኢብራሂም ዲአሎ የተባላ ሶፍትዌር አበልፃጊው በቀደሞው ስራ አስኪያጁ በአዲስ የኮምፒውተር ስርዓት የስራ ውሉ ባለመታደሱ ግለሰቡ በማሽኑ…
Read more

ፌስቡክ የሀሰት ዜናዎችን ከገጹ ላይ እንደማያጠፋ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፌስቡክ የሀሰት መረጃዎችን ከገፁ ላይ እንደማያነሳ አስታውቋል። ኩባንያው በብሪታኒያ “የሀሰት ዜና ጓደኛችን አይደለም” በሚል በማካሄድ ላይ በሚገኘው የማስታወቂያ ዘመቻ ላይ ነው ይህንን ያስታወቀው። ፌስቡክ በዚሁ ወቅት እንዳስታወቀው፥ “የሀሰት ዜናዎችን በገፁ ላይ የሚለቁ ሰዎች የተለየ አመለካከት ስላላቸው ነው፤ ስለዚህ የነዚህን ሰዎች ሀሳብ ከገፅ ላይ ማንሳት የመናገር ነፃነትን እንደመጋፋት ነው የሚቆጠረው…
Read more

የሰው አልባ አነስተኛ አውሮፕላኖች /ድሮኖች / ገመድ አልባ በይነ መረብ አገልግሎት እየተስፋፋ ነው

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 10፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሰው አልባ አነስተኛ አውሮፕላኖች /ድሮን / ገመድ አልባ በይነ መረብ አገልግሎት እድገት በፍጥነት እየተስፋፋ መሆኑ ተገለጸ። በፈረንጆቹ 2020 ከ13 በመቶ በላይ የሰው አልባ አነስተኛ አውሮፕላኖች /ድሮኖች / ሲም ካርዶችን በመውሰድ የገመድ አልባ በይነ መረብ አገለግሎትን ለማሻሻል እንደሚችሉ ተገልጿል። የሰው አልባ አነስተኛ አውሮፕላኖች /ድሮኖች / በተለያዩ ገበያ ተኮር አገልግሎት ላይ…
Read more

የግብጽ ፓርላማ ማህበራዊ የትስስር ገጾችን መቆጣጠር የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ አፀደቀ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 10 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ግብጽ ማህበራዊ የትስስር ገጾችን መከታተልና መቆጣጠር የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ አፀደቀች። በትናንትናው እለት በሃገሪቱ ፓርላማ የፀደቀው ረቂቅ አዋጅ፥ ከፍተኛ ተከታታይ ያሏቸው ግለሰቦችና ተቋማት ማህበራዊ የትስስር ገጾች በመንግስት አካላት ቁጥጥር እንዲደረግባቸው የሚያዝ ነው ተብሏል። በዚህ መሰረት በማህበራዊ ትስስር ገጾች ከ5 ሺህ በላይ ተከታዮች ያላቸው ግለሰቦች አድራሻ በሃገሪቱ…
Read more

ጎግል የስራ ማፈላለጊያ አገልግሎት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጎግል አዳዲስ ክፍት የስራ ቦታዎችን የማፈላለግ አገልግሎት መጀመሩ ተነግሯል። ግዙፉ የመረጃ ማፈላለጊያ የሆነው ጎግል በቀላሉ ከዋናው ገፁ ላይ ስራ ለማፈላለግ፣ የተሻለውን ለማመዛዘን እና ለስራው ማመልከት የሚያስችል አገልግሎት መጀመሩ ነው የተገለፀው። አገልግሎቱን ለማግኘት መድረግ የሚጠበቅብን በማፈላለጊያ ገጹ ላይ የምንፈልገውን የስራ አይነት ለምሳሌ “መምህርነት” በሚል ብቻ መጻፍ ሲሆን፥ ጎግል ከመምህርነት ጋር…
Read more

የስነፈለክ ባለሙያዎች በጁፒተር ዙሪያ አስር አዲስ ጨረቃዎችን አገኙ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ፣11፣2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የስነፈለክ ተመራማሪዎች በትልቋ ፕላኔት ጁፒተር ዙሪያ አስር አዳዲስ ፕላኔቶችን ማግኘታቸውን አስታወቁ፡፡ በዩናይትድ ስቴትስ መረጃው ይፋ ሲሆን ጁፒተር በጥቅሉ 79 ጨረቃዎች ያሏት ፕላኔት መሆኗን ነው ተመራማሪዎቹ የገለጹት፡፡ በዚህም ጁፒተር ከየትኛውም ፕላኔት በመላቅ በምህዋሩ ውስጥ ብዙ ጨረቃ ያላት ፕላኔት መሆኗ ተረጋግጧል፡፡ አሁን አዲስ የተገኙት ጨረቃዎች ከሌሎቹ አንጻር በመጠን ትንንሽ መሆናቸው ተነግሮዋል፡፡ ጁፒተር ከፀሐይ…
Read more

ለ120 ቀናት በአየር ላይ መቆየት የሚችል አውሮላን የሙከራ በረራውን አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 16፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለ120 ቀናት በአየር ላይ መቆየት የሚችለው አውሮላን የሙከራ በረራውን ማድረጉ ተግልጿል። ዘፔይር የተባለው አውሮፕላን በጸሃይ ሀይል የሚንቀሳቀስ ሲሆን፥ ለ120 ቀናት ያህል በአየር ላይ ለመቆየት እንደሚችል ነው የተገለጸው። አዲሱ አውሮፕላን ቀንቀን የጸሃይ ሀልይልን በመጠቀም የሚንቀሳቀስ ሲሆን፥ ማታ ማታ የሚጠቀምበትን ሀይል ቀን ቀን በመሰብሰብ የጸሀይ ሀይልን ብቻ የሚጠቀም መሆኑን ነው ዘገባው…
Read more

በሲንጋፖር የ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ግለሰቦች የጤና ነክ መረጃ ተበርብሯል

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 17 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) መረጃ በርባሪዎች በሲንጋፖር የማህበረሰብ ጤና አገልግሎት ማዕከል ላይ የመረጃ ምዝበራ ማድረሳቸው ተነገረ። መረጃ በርባሪወቹ ባደረሱት ጥቃት ሳቢያም የ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ግለሰቦች የጤና መረጃን በርብረዋል። የሲንጋፖር ጤና ጥበቃ መስሪያ ቤት ባለስልጣናት እንዳስታወቁት፥ የሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ሲዬን ሉንግ የጤና መረጃዎችም የመረጃ በርባሪዎቹ ሰለባ ሆነዋል። የጤና…
Read more

ፌስቡክ በቻይና ቢሮውን ለመክፈት አቅዷል

አዲስ አበባ፣ ሀምሌ፣18፣2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፌስቡክ አገልግሎቱን በማይሰጥባት ቻይና ትርፋማ በሆነው ገበያ ለመሳተፍ ፈቃድ በማግኘቱ ቢሮውን በቅርቡ እንደሚከፍተ ተገለፀ። ኩባንያው በቻይና የሚከፍተው ቢሮ ቻይናውያን አበልፃጊዎችና ስራ ፈጣሪዎችን ለመደገፍ የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል። በቻይና የሚከፈተው ይህ ቢሮ ለኩባንያው የመጀመሪያው እንደሚሆንም ነው የተነገረው። ቻይና በአለም አቀድ ደረጃ ከፍተኛ የሆነ የማህበራዊ መገናኛ ብዙሀን ንግድ ያለባት ቢሆንም ትዊተር፣ ፌስቡክ እና ዩቲዩብ…
Read more